Page 25 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 25
3. መልካም ቃላቶችን ለራስዎት ደጋግመው ይንገሩ፡፡
ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በጭንቀት፣ በሃዘን፣ በድብርት፣ እና በድብርት ውስጥ
ስንሆን የተወሰኑ ቃላቶችን መደጋገም ስሜቶቹን ይቀንሳል እንዲሁም መልካም አስተሳሰብን
ይጨምራል፣ ያረጋጋል እንዲሁም ትኩረትን ያክላል፡፡
ለምሳሌ፦ እኔ ጠንካራ ነኝ፣ ቆንጆ ነኝ፣ ጤናማ ነኝ፣ ማድረግ እችላለሁ፣ ይህም ደግሞ
ያልፋል፣ ውስጤ ሰላም ነው፣ ደስተኛ ነኝ፣ ሰላም አለኝ፣ ጤናማ ነኝ፣ ፍቅር ይገባኛል፣ እኔ
መልካም ነገሮች ይገቡኛል፣... ወዘተ የሚልሉትን መልካም ቃላቶች ለራሳችህን በቀን
በተደጋጋሚ መግለጽ በራስ መተማመናችንን በሚገባ ያዳብራል፡፡
አንዳንድ ሰዎች የመፅሃፍ ቅዱስ፣ የቆራን ወይም ሌሎች የእምነት መጽሃፍት ክፍሎችን
መደጋገም ያረጋጋናል፣ ያጽናናናል፣ መንፈሳችንን ያነቃቃልናል፣ እንዲሁም ያበረታታናል
ይላሉ፡፡
4. የምስጋና ማስታወሻ
ይሔ በጣም ቀላል ነገር ግን እጅግ ጠቃሚ ልምምድ ነው፡
፡ ይህንን ለማድረግ በቀላሉ የሚያስፈልገው አንድ
የማስታውሻ ደብተር አዘጋጅቶ በቀን ውስጥ ቢያንስ
አንድ የሚያመሰኑበትን ነገር በማስታወሻዎት ላይ ማኖር
ነው፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ያህል ቀንዎት እንዴት
እንደነበር ካጠነጠኑ በኋላ ያስታወሱትን ያህል የሚያመሰግኑባቸውን ነገሮች ይፃፉ፡፡ ይህንን
ልምድ ሁሌ ማታ ማታ ወደ አልጋ ከመሔድዎ በፊት ቢያደርጉት በህይወትዎ ደስተኛ እንዲሆኑ
ከመርዳቱም በላይ አላስፈላጊ አሉታዊ ሀሳቦችን ያስወግድሎታል፡፡
22