Page 29 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 29
8. ዝነጣ ለመንፈስ መታደስ
አንዳንድ ሰዎች ድባቴ እና ጭንቀት በሚሰማቸው
ወቅት ዘንጦና ለባብሶ መቀመጥ ወይም ከቤት
መውጣት በራስ የመተማመን ሰሜታችንን
ያጎለብትልናል ይላሉ፡፡ እርስዎም የሌሊት
ልብስዎን ሳያወልቁ ቀኑን ሙሉ ከማሳለፍ ይልቅ
ገላዎን ለቅለቅ ብለው ንጹህ ልብስ ቢለብሱ ፈጣን
የስሜት ለውጥ ሊያመጣልዎት ይችላል፡፡
አንዳንዶች ደግሞ ፀጉራቸውን ሲቆረጡ ወይንም
ሲሰሩ ተመሳሳይ የስሜት መሻሻልን ያሳያሉ፡፡
ምንም እንኳን ባሁኑ ጊዜ ከቤት መውጣት
የማንችል፣ ብዙ ወደሰራ የማንሔድ፣ እንዲሁም
ወደመዝናኛ ቦታ መሔድ የማንችል ቢሆንም ልክ
ሰራ እንዳለን ወይንም በፊት ጓደኞቻችንን ስናገኝ
እንደምናረገው ሁሉ በጠዋት ተነስተን ዘንጠንና
ተስተካክለን ብንቀመጥ ቀናችን የበራ ይሆናል፡፡
26