Page 33 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 33
የሚያስከትሉ ምግቦችን፣ ጣፋጭና ስኳር የበዛባቸው ምግቦችን ያዘወትራሉ፡፡ ነገር ግን ይህን
ለተለያዩ እንደ ስኳር፣ ግፊት፣ የልብ በሽታ የመሳሰሉት በሽታዎ እንድንጋለጥ
ከማድረጋቸውም በተጨማሪ የጭንቀትና የድብርት መጠንን ይጨምሩብናል፡፡
በተቃራኒው ደግሞ አንዳንድ ሰዎች ጭንቀት
ሲይዛቸው የምግብ ፍላጎታቸው ስለሚቆለፍ
ምንም አይነት ምግብ መመገብ አይችሉም፡፡
በዚህም የተነሳ ለክብደት መቀነስ እንዲሁም በሽታ
የመከላከል አቅማቸው ከመዳከሙ የተነሳ ለብዙ
በሽታዎች ሊጋለጡ ይቸላሉ፡፡ ይህ ደግሞ አቅምና
ጉልበት በማሳጣት የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን እንዳያከናውኑ እክል ይሆንባቸዋል፡፡
በተቻለን መጠን አቀምን የሚገነቡና ለጤና ተስማሚ የሆኑ እንደ ባቄላ፣ ሽንብራ፣ አደንጓሬ፣
ምስር የመሳሰሉትን ጥራ ጥሬዎች፣ እንደ ጎመን፣ ቆስጣ፣ ብሮኮሊ የመሳሰሉትን አርንጓዴ
ቅጥል ያላቸውን አትክልቶች፣ ብርትኳን፣ ሙዝ፣ አቮካዶ የመሳሰሉትን ፍራፍሬዎች፣ ኦቾሎኒ፣
ተልባ፣ ሰሊጥ ያሉ የቅባት እህሎችን፣ እንዲሁም ነጭ ሽንኩርት፣ ዝንጅብል፣ ቃሪያ፣ እርድ
የምሰሉትን ቅመማ ቅመሞች መመገብ ለሰውነትና አእምሮአዊ ጤና እጅግ ተገቢ ነው፡፡
30