Page 21 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 21
ከኮቪድ 19 ጋር በተዛመደ ጭንቀትና ውጥረትን
ለማስተንፈስ የሚረዱ መንገዶች
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዘዴዎች ከኮቪድ 19 ምክንያት የሚደርሱብንን የጭንቀትና ይስጋት
ውጥረቶችን ለመቋቋም ይረዱናል፡፡
1. ትኩረትዎን ትንፋሽዎት ላይ ማድረግን ይለማመዱ
ይህ መልመጃ በጣም ቀላል ሲሆን በማንኛውም
ሰዓትና ቦታ የድብርት፣ የጭንቀት፣ የድካም፣ የንዴት
እንዲሁም ደህና ያለመሆን ስሜት ሲሰማዎ
በመተንፈስ ብቻ ራስዎትን እንዲያረጋጉ ይረዳል፡፡
ይህንን መልመጃ ተቀምጠው ወይንም ተኝተው
መተግበር ይችላሉ፡፡ ዋናው ማተኮር የሚያስፈልገው
የሚመችዎትን፣ ፀጥታ የሰፈነበትን ቦታ ይምረጡ፡፡ ትኩረትዎ እንዳይሰረቅ አይንዎን
ቢጨፍኑ ይመረጣል፡፡ ሲቀመጡ ወንበሩ ላይ ወገብዎን ቀጥ አድርገው ይቀመጡ፡፡ እግረዎን
ሳያነባብሩ የእግር መዳፍዎን ወለሉ ላይ ሙሉ በሙሉ መሬት ላይ ማሳረፍ፡፡
1. ልምምዱን ለመጀመር በአፍንጫዎ ውስጥ ለ 3 ሰከንዶች ያህል በጥልቀት አየር ወደ ውስጥ ይውሰዱ
2. ወደ ውስጥ ያስገቡትን አየር ለ 2 ሰከንዶች ያህል ወደውስጥ ይያዙት
3. በመጨረሻም የያዙትን አየር በአፍዎት ለ 4 ሰከንዶች በቀስታ ወደውጪ ይልቀቁት ፡፡
4. ይህንን ልምምድ ትኩረትዎን ትንፋሽዎት ላይ በማድረግ ከ5 እስከ አስር ደቂቃ ያህል ይተንፍሱ፡፡
18