Page 16 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 16
የአእምሮ ጤናዎ እና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ
ጭንቀት፣ ስጋት እና ውጥረት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ
ወቅት
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በብዙ ሰዎች ላይ አስጨናቂ እና አስደንጋጭ ሊሆን ይችላል። ይህ አዲስ
በሽታ በአዋቂዎችም ሆነ በልጆች ላይ ከባድ ፍርሃት እና ጭንቀትን እንዲሁም የስሜትን
መረበሽን ሊያስከትል ይችላል ፡፡
ኮቪድ 19 ወረርሽኝ በእያንዳንዱ ሰው ላይ በተለያየ መንገድ ጫና ያሳድራል ነገር ግን በብዙ
ሰዎች ላይ በተመሳሳይ መልኩ እየደረሰ ያለው በአእምሮ ጤና ላይ የሚታየው ተፅእኖ ነው::
ወረርሽኙ ብዙ ሰዎች ህይወታቸው ላይ ጥርጣሬንና አለመተማመንን እንዲሁም
አለመረጋጋትን በመፍጠሩ ብዙ ሰዎች ለከፍተኛ ጭንቀት ፣ ለድብርት ፣ ለብስጭት ፣ ቁጣ ፣
ለፍርሃት እና ሌሎችንም የአእምሮ ጤና መቃወስ ተጋልጠዋል፡፡
በተለይም ደግሞ የማህበራዊ ቅርርቦሽን ማቆም የመሰሉ የማህበረሰብ ጤና እርምጃዎች
ሰዎች የመነጠል እና የብቸኝነት ስሜቶች እንዲያጠቋቸው ያደርጋል፡፡
13