Page 13 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 13
ክፍሎችን በጋራ የሚጋሩ ከሆነ ግን በክፍሎች ሁሉ ውስጥ
ጥሩ አየር ዝውውር እንዲኖር በሮችንና መስኮቶችን
በመክፈት ያረጋግጡ፡፡ ይህንን ማድረግ በአየር ላይ ከምራቅ
ጋር የተረጩና ኮቪድ 19ን የያዙትን ነጠብጣቦች ከአየሩ ላይ
ለማስወገድ ይረዳል፡፡
የሽንት ቤት ወረቀት (ሶፍት)፣ ሳሙና፣ ፎጣ እና ሳኒታይዝር
የመሳሰሉትን የግል ንፅህና መጠበቂያዎች አሟልተው
ይስጡት፡፡
አላስፈላጊ የዘመድና የጎረቤት ጠያቂዎች እና ጎብኝዎች እንዳይኖሩ ያድርጉ፡፡ በተለይ
በቫይረሱ ለመያዝ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸውን ሰዎች ያርቁ፡፡
ተለያይተው ይመገቡ
በተለዩ ክፍሎች ወይም አካባቢዎች ይመገቡ፡፡ ከተቻለ የታመመው ሰው በክፍላቸው ውስጥ
ወይንም አልጋቸው ላይ በመሆን መብላት ወይም መመገብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሙቅ ውሃን
በመጠቀም ሳህኖቹን እና ዕቃዎችን ያጥቡ-ማንኛውንም የሚጠቀሙባቸውን ሳህኖቹን፣
ኩባያዎች እና ዕቃዎችን ሲያጥቡ በሳሙና እና በሙቅ ውሃ እንዲሆን ይመረጣል፡፡
10