Page 9 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 9
ለይቶ ማቆያ/ ኳራንቲን ምንድን ነው?
ኳራንቲን ማለት በተላላፊ በሽታ የተጋለጡ ሰዎች ወይም ተላላፊ ህመም ካለበት ሰዉ ጋራ
ቅርበት እና ንክኪ የነበራቸዉ ሰዎች በበሽታው መያዝ አለመያዛቸው እስኪታወቅ ድረስ
እንቅስቃሴያቸውን የሚገድብና ከሌሎች ሰዎች ጋራ እነዳይቀላቀሉ የሚያደርግ ሂደት ነው፡፡
ኳራንቲን ለጊዜዉ የህመም ምልክት ያልታየባቸዉ ወይንም የተረጋገጠ የህክምና ውጤት
ላይ ያልደረሱ ሰዎች በሽታዉን ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳያስተላልፉ ለማድረግ ይረዳል፡፡
ኳራንቲን በለይቶ ማቆያ ማዕከሎች ወይንም በመኖሪያ ቤታችን ውስጥ ሊደረግ ይችላል፡፡
ኳራንቲን ለማድረግ የሚውስደው ቀናት 14 ቀናት ብቻ ነው፡፡
ሰዎች በኳራንቲን በሚቆዩበት ወቅት የተለያዩ ስሜት ላይ ጫና የሚፈጥሩ ነገሮች
ሊያጋጥሟቸው ይችላል፡፡
ከነዚሁም መካከል ለምሳሌ:-
ስጋት፡ ለእራሳቸው እና ለሌሎች ጤና መታወክ ጠንቅ እንዳይሆኑ መስጋት
ከሌሎች ሰዎች ጋራ ያለማህበራዊና አከላዊ ግንኙነት በመቋረጡ ምክንያት
መሰላቸትና ተስፋ መቁረጥ
በኳራንቲን ማእከሎች ውስጥ በቂ የመሰረታዊ ፍላጎቶች ባለመሟላታቸው ምከንያት
መበሳጨት ለምሳሌ (ምግብ፣ ዉሃ፤ አልባሳት እና የመጠለያአቅርቦቶችን በበቂ ሁኔታ
አለማግኘት)
ኳራቲንን በተመለከተ ስለ አላማው በቂ መረጃ አለማግኘት
ጭንቀት፣ ድንጋጤ፣ ድብርት፣ የመዋረድ ስሜት፣ ፍርሃት፤ ሃዘንተኝነት፤ ብቸኝነት፤
ንዴት፤ የእንቅልፍ እጦት፤ የመሳሰሉት ስሜቶችን ማስተናገድ
6