Page 4 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 4
መሠረታዊ የኮቪድ 19 መረጃዎች
ኮቪድ 19 ምንድነው?
ኮቪድ-19 ኮሮና በተባለ ቫይረስ ምክያት የሚከሰት በሽታ ሲሆን የኮቪድ-19 (COVID-19)
ምህጻረ ቃሉ ሲተረጎም፦ 'ኮ' ኮሮና ፣ 'ቪ' ቫይረስ ፣ እና 'ዲ' ደግሞ disease ወይም በሽታን
ያመለክታል፡፡ ይህ ቫይረስ አንዳንድ የተለመዱ ጉንፋን ዓይነቶች ጋር የተገናኘ አዲስ ተላላፊ
ቫይረስ ነው፡፡
ኮቪድ 19 ከሰው ወደ ሰው እንዴት ይተላለፋል?
ኮቪድ 19 በቫይረሱ የተያዘ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ ከአፍና
ከአፍንጫ በሚወጡ በዐይን የማይታዩ የምራቅ
ነጠብጣቦች አማካኝነት ይተላልፋል፡፡
ስለሆነም የመተንፈሻ አካል ሰርዐተ ልምምዶችን
ተግባራዊ ማድረግ ቫይረሱ ከሰው ወደሰው
እንዳይተላለፍ በከፍተኛ ሁኔታ ይረዳል ለምሳሌ፦
በሚያስነጥሱበት ወይም በሚያስሉበት ወቅት
አፍና አፍንጫን ክንድዎን በማጠፍ መሸፈን ወይንም በመሀረብ መሸፈን አስፈላጊ ነው፡፡
1