Page 5 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 5

ኮቪድ 19ኝን ለመከላከል ምን ማድረግ ይቻላል?




               ኮቪድ  19  ለመከላከል  እና  ሰርጭቱን  ለመቀነስ  በጣም  የተሻለው  አማራጭ  ስለ

               ቫይረሱ  ፣  ስለሚያስከትለው  በሽታ  እና  እንዴት  እንደሚሰራጭ  እና  እንዴት

               መከላከል እንደሚቻል በሚገባ መረጃ መሰብሰብ አስፈላጊ ነው ፡፡



               እንዲሁም እጅዎን ቶሎ ቶሎ በሚገባ በመታጠብ ወይም በአልኮል የተሰሩ ማጽጃ

               ፈሳሾች  በመጠቀም  እጅዎትን  እንዲሁም  የበር  መዝጊያዎችንና  የእጅ  ንክኪ


               የሚበዛባቸውን መሳሪያዎች በሚገባ በማጽዳት፤ እና የፊት ንክኪን በማስወገድ


               ኮቪድ 19ንን መከላከል ይቻላል፡፡


               ከዚህ በተጨማሪ  የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን በ መታጠቅ ቫይረሱ


               እንዳይተላልፍብን እና እኛም ተይዘን ከሆነ ወደሌሎች እንዳናስተላልፍ ይረዳናል፡፡


               ሌላኛው  የአለም  የጤና  ድርጅት  እንደመከላከያ  መንገድ  ያስቀመጠው  ዋነኛ


               መንገድ  ደግሞ  አካላዊ  ርቅትን  መጠበቅ  ነው፡፡  በተለይም  በሀገራችን

               የተለመደው መሳሳምና መጨባበጥ ፈፅሞ ማስቀረት አስፈላጊ ነው፡፡


















                                     ደህንነቱን የጠበቀ ሰላምታን እንለማመድ





                                                              2
   1   2   3   4   5   6   7   8   9   10