Page 11 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 11

 ሰዎች በኮቪድ 19  ተይዘው በቤታቸው ውስጥ ራሳቸውን ለይተው


                   በሚቀመጡበት  ወቅት  የተለያዩ  ነገሮች  ሊያስፈልጓቸው  ይችላሉ፡፡

                   ስለዚህም  የተለያዩ  የቤት  ውስጥ  ሸቀጣ  ሸቀጦችን  በማሟላት፣


                   መድሃኒቶችን በመግዛትና ወደነሱ በማድረስ፣ አትክልቶችንና የተለያዩ

                   አስቤዛዎችን በመግዛት ብናግዛቸው ከባድ ሸክምን እናቀልላቸዋለን፡፡





               የማስጠንቀቅ ምልክቶችን በሚገባ ይከታተሉ


               የህኪም  ቤት  ወይንም  የዶክተር                ስልክ  ቁጥር  በቅርብዎ  በመያዝ  ታማሚው                      ህመሙ


               እየባሰባቸው  ከሄደ  ለሐኪማቸው  ፣  ለሆስፒታል  ወይንም


               ድንገተኛ ህክምና በ8335 ወይንም 952 ላይ ይደውሉ ፡፡


               የኮቪድ 19ን የአደጋ ጊዜ  ማስጠንቀቂያ ምልክቶችን በሚገባ


               በማስተዋል  አንድ ሰው ከነዚህ በታች የሚገኙትን ምልክቶች

               አንዱን ካሳየ ወዲያውኑ የድንገተኛ ሕክምናን ይፈልጉ፦




                    የመተንፈስ ችግር
                    በደረት ውስጥ የማያቋርጥ ህመም ወይም ግፊት


                    ግራ መጋባት

                    ከእንቅልፍ መንቃት አለመቻል


                    የከንፈር ወይንም የፊት ቀለም ወደ ጠቋር ሰማያዊነት


                       መቀየር


               እነዚህ  ዝርዝር  ምልክቶች  የተሟሉ  ስላልሆኑ  ለአንዳንድ  ለሚያስተውሏቸው  ከበድ  ያሉ

               ምልክቶች የህክምና ባለሞያዎችን ያማክሩ፡፡




                                                              8
   6   7   8   9   10   11   12   13   14   15   16