Page 42 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 42

ከዚህ በታች በቀላሉ ሊያከናውኗቸው የሚችሏቸው የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች በምሳሌነት


               ተጠቅሰዋል፦



               የእግር ጉዞ ትናንሽ እና ጠባብ ክፍሎች እና ቦታዎች ላይ ቢሆን እንኳን  በእግር ወዲህ ወዲያ


               ማድረግ  አካል  ብቻ  ሳይሆን  መንፈስም  ንቁ  ሆኖ  እንዲቀጥል  ይረዳል።  ስልክ  ላይ  ሲሆኑ

               ተቀምጠው ከሚያወሩ ይልቅ በቤት ውስጥም ሆነ በውጪ ወዲህ ወዲያ ማለቱ ያዋጣል፡፡


               ረዘም ያለ የእግር ጉዞ ከቤትዎ ውጪ ለማድረግ ካሰቡ ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

               ለማድረግ ወደ ውጭ ለመሄድ ከወሰኑ ከሌሎች ሰዎች ቢያንስ አንድ ሜትር ርቀት መራቅዎን


               ያረጋግጡ ፡፡



               ዮጋ  ተጣጣፊነት  ይጨምራል፣  የጡንቻ  ጥንካሬን  ያሻሽላል፣  የተሻሻለ  መተንፈሻ  ሂደትን


               ይፈጥራል፣ ጉልበትን ያሻሽላል፣                የምግብ ዑደትን ያስተካክላል፣ ክብደት መቀነስ ይረዳል፣

               የልብና የደም ዝውውር ጤናን ያስተካክላል፣ ያማረ አቋምን ይሰጠናል፣ ወ.ዘ.ተ...፡፡



               አጭር  ሩጫ  ስብን  ያቃጥላል፣  መሮጥ  ጥሩ  ስሜት  እንዲሰማዎት  ያደርግዎታል፣  ቶሎ

               ትንፋሽዎትን  መሰብሰብ  እንዲችሉ  ያድርግዎታል፣  እንቅልፍን  ያሻሻላል፣  ያማረ  አቋምን


               ይሰጣል፣ ረጅም እድሜን ይጨምራል፣  ወ.ዘ.ተ...፡፡


               የአካል  ብቃት  መተግበሪያ  (app)  ያውርዱ  የአካል  ብቃት  መተግበሪያዎች  መጠቀም


               የተለያዩ  ጥቅም  አሉት፡፡  ከነዚህም  መሃል፦  አመጋገብዎን  በቀላሉ  እንዲቆጣጠሩ  ይረዳል፣


               ሂደትዎን  እንዲከታተሉ  ይረዳል፣                ነፃ  የጤና  እና  የአካል  ብቃት  ምክሮችን  ይለግስዎታል፣

               የእግርዎን እርምጃዎች ይቆጥራል፣  ተነሳሽነት ይጨምራል ወ.ዘ.ተ...።













                                                             39
   37   38   39   40   41   42   43   44   45   46   47