Page 46 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 46
ወንበሩን ማጥቀስ
እግሮችዎን ከወንበሩ ግማሽ ሜትር ያህል አርቀው
የወንበሩን መቀመጫ አጥብቀው ይያዙ ፡፡
ወገብዎን ወደ መሬት ዝቅ ሲያደርጉ እጆችዎንም
አብረው ይጠፉ፡፡ በመቀጣልም ወደላይ ከፍ ሲሉ
ስዕሉ ላይ እንደሚያመላክተው እጆችዎንም
ይዘርጉ፡፡ ይህንን እንቅስቃሴ ከ10-15 ጊዜያት ይደጋግሙ ፡፡ ይህ መልመጃ በላይኛውጀርባ
ላይ ያሉ ጡንቻዎችንና የእጅ ጡንቻዎችን ለማጠናከር ይረዳል፡፡
የደረት መሰንጠቂያ
ጣቶችዎን ከጀርባዎ ኋላ ወጥረው ያያይዙ ደረትዎንም ወደፊት
ይግፉ፡፡ ይህንን አቋም እንደያዙ ለ 20 ሴከንዶች ያህል ይቆዩ፡፡ ይህ
እንቅስቃሴ ደረትን እና ትከሻዎን ያራዝማል ፡፡ በቀን ውስጥ
ውጥረት እና መተሳሰር በተሰማን ሰአት ሁሉ ይህንን እንቅስቃሴ
ማድረግ እንችላለን፡፡
43