Page 117 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 117

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ



             ማጠቃለያ

                     ሃገራችን ኢትዮጵያ፣ የበርካታ ምዕተ ዓመታት የተጻፈ ታሪክ ካላቸው ጥቂት
             የአፍሪካ  ሃገሮች  ውስጥ  አንዷ  መሆና  ይነገራል።  ለዚህም፣  በበርካታ  ግንባር  ቀደም
             ዩኒቨርሲቲዎች እና ዓለም አቀፍ የታሪክ ጥናት ማእከሎች የሚካሄዱ ጥናቶች እና የሚገኙ
             የታሪክ ሰነዶች እንደ ማረጋገጫ ይቀርባሉ። ይህ እንዳለ ሆኖ፣ በዘመናዊ የሃገረ መንግሥት
             ምስረታ ሂደት ያላት ታሪክ ነጻነታቸውን በቅርቡ ከተቀዳጁ ሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች ብዙም
             የተለየ  አይደለም።  በቅርቡ  የሃገራችን  የፖለቲካ  ታሪክ  ውስጥ  በለውጥ  ቀስቃሽነት
             የሚጠቀሰው የ1953 መፈንቅለ መንግስት ሙከራ በርካታ የአፍሪካ ሃገሮች ከቅኝ ተገዢነት
             ነጻ  ከወጡበት  ዓመት  ጋር  መገጣጠሙ  ከላይ  የተጠቀሰውን  ምልከታ  ያጠናክረዋል።
             እንዳብዛኞቹ የአፍሪካ ሃገሮች፣ ኢትዮጵያም ባለፉት ስልሳ ዓመታት በተለያዩ የፖለቲካ
             ሙከራዎች  እና  ሂደቶች  ውስጥ  አልፋለች።  ነገር  ግን፣  እነኚህ  ከፍተኛ  መስዋእትነት
             የተከፈለባቸው  ሙከራዎች  እና  ሂደቶች  የመላ  ህዝቦቻችን  ተቀባይነት  ወዳለው  ሃገረ
             መንግሥት ምስረታ ሊያሸጋግፘት አልቻሉም። ዛሬ ሃገሪቱ ካሉባት ውስብስብ የኢኮኖሚ፣
             ማህበራዊ፣  ከባቢያዊ፣  ፖለቲካዊ  እና  ንፍቀ  ከባቢያዊ  ፈተናዎች  አኳያ  ሌላ  ያልተሳካ
             የፖለቲካ ሙከራ የመሻገር እድሏ እጅግ የመነመነ መሆኑን መገመት ይቻላል። ስለሆነም፣
             ከፊት  ለፊታችን  ያለውን  የለውጥ  እና  ሽግግር  ዕድል  የተሳካ  ለማድረግ  ሁሉም  ወገን
             የሚቻለውን ርብርብ ማድረግ ይጠበቅበታል።
                     ይህ  ጥረት  የተሳካ  እንዲሆን፣  የችግሮቻቻን  መሰረታዊ  ምንጮች  ባግባቡ
             መረዳት  እና  ባላፉት  ስልሳ  ዓመታት  ካለፍንባቸው  የፖለቲካ  ምስቅልቅሎች  ልንማር
             የሚገባንን  ትምህርት  መቅሰም  ይኖርብናል።  ከዚህ  በተጨማሪም፣  የምንገኝበትን  የሃያ
             አንደኛውን ክፍለ ዘመን ውስብስብ ፈተናዎች እና እድሎች ጠንቅቆ መረዳት እና ፈተናዎቹ
             ሊያስከትሉ የሚችሉትን ጉዳት ለመቀነስ እና እድሎቹን ባግባቡ ለመጠቀም የሚያስችሉንን
             አቅጣጫዎች መተለም ይገባል። ይህንን ሁሉ ለማድረግ፣ ጊዜውን በሚመጥን እውቀት
             መታጠቅ እና መመራት አስፈላጊ ነው። በዚህ ረገድ፣ ውስብስብ ችግሮችን ለመተንተን እና
             መፍትሄ  ለመሻት  አጋዥ  በሆነው  ምህዳራዊ  አስተሳሰብ  መመራት  ከፍተኛ  ጠቀሜታ
             አንደሚኖረው ይታመናል። በዚህ መጽሃፍ፣ የምህዳራዊ አስተሳሰብ ታሪካዊ አመጣጡን
             እና መስረታዊ መርሆዎቹን ከማቅረብ ባሻገር የኢትዮጵያን ፖለቲካ መሰረታዊ ህመሞች
             ከዚሁ አኳያ ለመተንተን እና አመላካች መፍትሄ ለመጠቆም ተሞክሯል። ምንም እንኳን፣
             የቀረቡትን  ሃሳቦች  የተሟላ  ለማድረግ  ጥረት  የተደረገ  ቢሆንም፣  ትንተናዎቹም  ሆነ
             የመፍትሄ  ሃሳቦቹ  ከአመላካችነት  የዘለለ  ድርሻ  እንዳይሰጣቸው  ጥንቃቄ  ማድረግ
             ያስፈልጋል።  በመሆኑም፣  በመጽሃፉ  ውስጥ  የቀረቡትን  ሃሳቦች  ይበልጥ  መፈተሽ  እና
             ተለዋዋጭ ከሆነው ሃገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ እውነታ ጋር አዛምዶ መተንተን ከሁሉም
             ወገን የሚጠበቅ ድርሻ ይሆናል።


                                                                       109
   112   113   114   115   116   117   118   119   120   121   122