Page 114 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 114
ደስታ መብራቱ
ዋስትና የሚያረጋግጡ የሁለንተናዊ ደህንነት ኢኮኖሚ (Wellebing economy)
ፖሊሲዎችን ለመቅረጽና ለመተግበር መጣር ይኖርባቸዋል።
xiii. የ ‘ምትሃታዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲ’ ሌላው መገለጫው ተግባራዊነታቸው
በአብዛኛው አጠያያቂ የሆኑ ዓመታዊ፣ የአምስት ዐመት እና አንዳንድ ጊዜም
የአስር ዓመት እቅድ የሚመስሉ ‘ያልታቀዱ እቅዶችን’ (unplanned planning)
ማውጣታቸው ነው። ይሀም፣ ከፍተኛ ለሆነ የሃብት ብክነት እንዲጋለጡ
አድርጓቸዋል።
xiv. እነኚህን ችግሮች ለማወስገድ፣ ከላይ ወደ ታች የሚወርድ አመላካች ዕቅድን
(indicative planning) ከታች ወደላይ ከሚመግብ እና ህዝብን ካካተተ
የአፈጻጸም ዕቅድ (operational planning) ጋር ማዋሃድ አካታች እና ዘላቂ
የሆነ ልማት ለማምጣት እጅግ አስፈላጊ ነው። እንዲህ ዓይነቱ የዕቅድ አወጣጥ
እና አፈጻጸም ‘የሽመና እቅድ’ (discursive planning) ተብሎ ይታወቃል።
xv. አጠቃላይ የመልካም አስተዳደር (good governance) እጦት፣ ኢትዮጵያን
ጨምሮ፣ የብዙዎቹ በማደግ ላይ ያሉ ሃገሮች ችግር መሆኑ ተደጋግሞ የተነገረ
ነው። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አካታች እና ዘላቂ ልማትን ለማምጣት ተጨማሪ
የልማት መልካም አስተዳደር እርምጃዎችን መመልከት ተገቢ ይሆናል።
xvi. ለዚህም የመጀመሪያው መነሻ፣ የሃገሪቱ የልማት ጥረት መሰረታዊ ግብ፣ ጥቅል
ሃገራዊ ምርትን (Gross Doemstic Product (GDP)) እና የነፍስ ወከፍ ገቢን
(per capita income) ከማሳደግ ባሻገር፣ የህዝቦችን ሁለንተናዊ የኑሮ ደህንነት
(wellbeing) ማረጋገጥ ሊሆን ይገባዋል።
xvii. እንዲህ ዓይነቱ የልማት አስተዳደር፣ በተወሰኑ ከተሞች አካባቢ ከሚከማቹ
የኢንዱስትሪ እና ልማት ማዕከሎች ባሻገር ለበርካቶች የስራ ዕድል እና የኑሮ
ዋስትና ሊሰጡ የሚችሉ እና ከየአካባቢው የተፈጥሮ ሃብት እና መሰረታዊ
ፍላጎት ጋር የተስማሙ፣ ያልተከማቹ፣ ነገር ግን እርስ በእርስ የተሳሰሩ የኢኮኖሚ
መረቦች (distributed economy networks) እንዲስፋፉ ያደርጋል።
xviii. ይህንን በማድረግም፣ ፍትሃዊ የሆነ የልማት ተደራሽነትን ከማረጋገጥም በላይ
በየአካባቢው ባለ የተፈጥሮ ሃብት ላይ የሚደርሱ የልማት ተጽእኖዎችን
ባካባቢው የተፈጥሮ ሃብት የመሸከም እና የማዋሃድ አቅም (carrying and
assimilation capacity) ክልል እንዲስተናገድ ማድረግ ይቻላል።
xix. የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ኢኮኖሚ ዋነኛው መለያ ከምንግዜውም በላይ
በዕውቀት እና መረጃ የበላይነት የሚወሰን መሆኑ ነው። በእንዲህ ዓይነት
ኢኮኖሚ ውስጥ አሸናፊ ሆኖ ለመገኘት ለዘመኑ የሚመጥን ክህሎትን
ያለማቋረጥ ማዳበር እና ማበልጸግ ያስፈልጋል። ይህም፣ በመደበኛው ትምህርት
የምክንያታዊነት አስተሳሰብን (critical thinking) እንዲያዳብሩ ማድረግ እና
በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍም በምህዳራዊ አስተሳሰብ (systems thinking) ላይ
የተመረኮዙ መፍትሔዎችን ለማፍለቅ የሚያስችላቸውን ክህሎት እንዲያዳብሩ
ማድረግ ተገቢ ነው።