Page 113 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 113

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


               vi.   ስለዚህም፣  ሃገሪቱ  የምትተገብራቸው  የልማት  እቅዶች  በሙሉ፣  የሃገሪቱን
                     የተፈጥሮ ሃብት መሰረት (ecological foundation) ይበልጥ የሚያጠናክሩ፣
                     ምርታማ  የሆነ  የተፈጥሮ  ሃብት  አጠቃቀምን  (resource  efficiency)
                     የሚያረጋግጡ፣ እና የሃገሪቱን ብዝሐ ህይወት የሚያበራክቱ ሊሆኑ ይገባል።
               vii.   ከሃያኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አንስቶ የዓለማችን የህዝብ ብዛት በብዙ እጥፍ
                     አድጎ እ.ኤ.አ. በ2019 7.7 ቢሊዮን ሲደርስ፣ ይኽው ቁጥር እ.አ.አ. በ2030 8.5
                     ቢሊዮን እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ2050 ወደ 9.7 ቢሊዮን እንደሚደርስ ተገምቷል።
                     በተመሳሳዩ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት እ.አ.አ. በ 2017፣ 105 ሚሊዮን እንደነበረ
                     የሚገመት ሲሆን፣ ይህ ቁጥር እ.አ.አ. በ 2050 190 ሚሊዮን እና እ.ኤ.አ. በ
                     2100 ደግሞ 250 ሚሊዮን እንደሚደርስ ተገምቷል። ይህንን ከፍተኛ የህዝብ
                     ቁጥር እድገት ግምት ውስጥ ያስገባ የልማት ራዕይ ማበልጸግ የሃገሪቱን ልማት
                     ዘላቂነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው።
              viii.   ሃገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ በማደግ ላይ የሚገኙ ሃገሮች ያለፉት ሶስት
                     የኢንዱስትሪ  አብዮቶች  በተሳታፊነት  ሳይሆን  በበዪ  ተመልካችነት
                     አሳልፈውታል። በአሁኑ ወቅት ዓለማችን የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ዋነኛ
                     መለያ ወደሆነው አራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት በመገስገስ ላይ ይገኛል።
               ix.   ሃገራችን ኢትዮጵያ ከዚህ ኢንዱስትሪ አብዮት በዪ ተመልካችነት እንድትድን
                     ከተፈለገ  የትኛውንም  የኢኮኖሚ  ዘርፍ  ለማሳደግ  የሚወጡ  ፖሊሲዎች  እና
                     ስልቶች፣  የአራተኛውን  የኢንዱስትሪ  አብዮት  ፈተናዎችን  በሚቀንስ  እና
                     እድሎቹን በሚያሰፋ መልኩ ሊቀረጹ እና ሊተገበሩ ይገባል።
                x.   በዓለም አቀፍ የገንዘብ፣ የፋይናንስ እና የንግድ ተቋማት አማካኝነት የተራመደው
                     የኢኮኖሚ  ሉላዊነት  በአብዛኛው  የበለጸጉ  ሃገሮችን  የኢኮኖሚ  ተጠቃሚነት
                     በሚያረጋግጥ መልኩ ተቀርጾ የተተገበረ በመሆኑ በማደግ ላይ የሚገኙ ሃገሮችን
                     ለከፍተኛ ቀውስ ዳርጓቸዋል።  ይህ አካሄድ አሁንም ሰወር ባለ (subtle) መልኩ
                     የቀጠለ ሲሆን ከመረጃ እና ተግባቦት ቴክኖሎጂ እድገት ጋር ተያይዞ የመጣው
                     የዕውቀት እና መረጃ ሉላዊነትም ተጨምሮበታል።
               xi.   እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሃገሮች የኢኮኖሚ ሉላዊነት ሊያስከትል የሚችለውን ጎጂ
                     ተጽእኖ ከመቋቋም ባሻገር ከዕውቀት እና መረጃ ሉላዊነት የሚገኘውን መልካም
                     እድሎች  ለሃገሮቻቸው  አካታች  እና  ዘላቂ  ልማት  እንዲያገለግሉ  የሚያስችሉ
                     ብልህነት  ላይ  የተመስረቱ  ፖሊሲዎችን  (smart  policies)  መተግበር
                     ይኖርባቸዋል።
               xii.   በአንድ ታዋቂ ፓን አፍሪካዊ ምሁር እንደተባለው፣ ብዙዎቹ የአፍሪካ ሃገሮች
                     የሚያራምዷቸው  የኢኮኖሚ  ፖሊሲዎች  ከሃገራዊ  እውነታ  እና  ፍላጎት  ጋር
                     ያልተጣጣሙ  በመሆናቸው  በምትሃታዊ  የኢኮኖሚ  ፍልስፍና  (Voodoo
                     economics) የተቃኙ አስመስሏቸዋል ። ከዚህ አይነት አዙሪት ለመውጣት፣
                     እንደ  ኢትዮጵያ  ያሉ  ሃገሮች፣  ሃገራዊውን  ፍላጎቶች  እና  ሃብቶች  ከዓለም
                     አቀፋዊው እድሎች እና ፈተናዎች ጋር በማጣጣም የህዝቦችን መስረታዊ የኑሮ

                                                                       105
   108   109   110   111   112   113   114   115   116   117   118