Page 108 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 108

ደስታ መብራቱ


                 ከዚህ በተጨማሪም፣ በአራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት አማካኝነት የሚፈጠሩ
           የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በደንብ ተረድቶ ለአካታች እና ዘላቂ ልማት ማዋል የሚያስችለውን
           የሙያ እና የቴክኒክ ክህሎት ማዳበር ያስፈልጋል። ይህንን በማድረግ ሂደት ውስጥ፣ ከሀገር
           በቀል ዕውቀት ሊወሰዱ የሚችሉ ጠቃሚ አስተሳሰቦች እና ሂደቶች ለመማር እና ይህንንም
           ከዘመናዊው  የዕውቀት  መስኮች  ጋር  በማጣጣም  ሃገራዊ  እና  አካባቢያዊ  ችግሮችን
           ለመፍታት የሚያስችሉ መፍትሔዎች ማመንጨት እና መተግበር ሊበረታታ ይገባዋል።
           በጥቅሉ፣ ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመንን በአሸናፊነት ለመሻገር ሉላዊ የሆነውን የዕውቀት እና
           የመረጃ ፍሰት ሃገራዊ ከሆነው ልዩ ሁኔታ እና ፍላጎት ጋር በማዋሃድ ለመጠቀም እና
           ለመተግበር መዘጋጀት እጅግ አስፈላጊ ነው።
   103   104   105   106   107   108   109   110   111   112   113