Page 104 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 104

ደስታ መብራቱ


                  ስለሆነም፣ ሃገራችን ኢትዮጵያ ከዚህ የኢንዱስትሪ አብዮት የበዪ ተመካችነት
           እንድትድን ከተፈለገ የትኛውንም የኢኮኖሚ ዘርፍ ለማሳደግ የሚወጡ ፖሊሲዎች እና
           ስልቶች፣  የአራተኛውን  የኢንዱስትሪ  አብዮት  ፈተናዎችን  በሚቀንስ  እና  እድሎቹን
           በሚያሰፋ መልኩ ሊቀረጹ እና ሊተገበሩ ይገባል።

                  ሉላዊነት (Globalization)፡ ዛሬ ባለንበት ሁኔታ ስለሉላዊነት በምንነጋገርበት
           ጊዜ፣ በሚከተሉት ሁለት አይነት ሉላዊነት መሃል ያለውን ልዩነት እና አንድነት መረዳት
           ይጠቅማል። የመጀመሪያው እና በሃያኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ ከታዩት ዓለም
           አቀፋዊ ክስተቶች አንዱ እና ዋነኛው፣ በዓለም አቀፍ የገንዘብ፣ የፋይናንስ እና የንግድ
           ተቋማት አማካኝነት የተራመደው የኢኮኖሚ ሉላዊነት ነው። ይህ በነጻ ገበያ የኢኮኖሚ
           አስተሳሰብ የተቃኘው ሉላዊነት በአብዛኛው የበለጸጉ ሃገሮችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን
           በሚያረጋግጥ መልኩ ተቀርጾ የተተገበረ ነው። ለዚህም፣ እ.ኤ.አ. ከ 1970ዎቹ መጨረሻ
           አንስቶ  በመላው  ዓለም  የሚገኙ  በማደግ  ላይ  ያሉ  ሃገሮች  በግዴታ  እንዲተገብሯቸው
           የተደረጉትን  የመዋቅራዊ  ማሻሻያ  ፕሮግራሞችን  (structural  adjustment
           programmes) እና ያስከተሏቸውን መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ እና አካባቢያዊ
           ቀውሶች መመልከቱ በቂ ነው። ይህ አካሄድ አሁንም ሰወር ባለ (subtle) መልኩ የቀጠለ
           በመሆኑ፣ እንደኢትዮጵያ ያሉ ሃገሮች ተገቢውን የፖሊሲ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል።

                  ሁለተኛው ሉላዊነት፣ ከመረጃ እና ተግባቦት ቴክኖሎጂ እድገት ጋር ተያይዞ
           የመጣው የዕውቀት እና መረጃ ሉላዊነት ነው። ምንም እንኳን ይህ ዓይነቱ ሉላዊነት፣
           በመሰረታዊ ባህሪው ዕውቀት እና መረጃ ለሁሉም ሊዳረስ የሚችልበትን ሁኔታ የሚፈጥር
           ቢሆንም፣ የመረጃውንም ሆነ የዕውቀቱን ፍሰት በመቆጣጠር የግል ብልጽግናቸውን ወይም
           ያላቸውን  የበላይነት  ለማስጠበቅ  በሚሹ  ወገኖች  የመጠለፍ  እድሉ  ከፍተኛ  ነው።
           ስለዚህም፣  እንደ  ኢትዮጵያ  ያሉ  ሃገሮች  ከዕውቀት  እና  መረጃ  ሉላዊነት  የሚገኘውን
           መልካም  እድሎች  ለሃገሮቻቸው  አካታች  እና  ዘላቂ  ልማት  እንዲያገለግሉ  የሚስችሉ
           በብልህነት  ላይ  የተመስረቱ  ፖሊሲዎችን  (smart  policies)  መቅረጽና  መተግበር
           ይኖርባቸዋል።
   99   100   101   102   103   104   105   106   107   108   109