Page 99 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 99

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


              xiii.   ከዚህ በተጨማሪም፣ ከመወያያ ርዕስ መረጣ እስከ ጽሁፍ ዝግጅት፣ አቀራረብ
                     እና  የውይይት  አደረጃጀት  ድረስ  ያሉትን  ሂደቶች  በጥንቃቄ  መተለም  እና
                     ማዘጋጀትን  ይጠይቃል።  የመወያያ  ርዕስ  መረጣን  በሚመለከት  ለብሔራዊ
                     መግባባት ውይይት የሚመረጡ ርዕሶች የዲምክራሲያዊ መፎካከሪያ ምህዳሩን
                     ጤናማነት ለማጠናከር አስፈላጊ የሆኑ የመተባበሪያ ርዕሶች ሊሆኑ ይገባቸዋል።
              xiv.   ከዚህ በተጨማሪ፣ ለብሔራዊ መግባባት ውይይት የሚቀርቡ ጽሁፎች በአንድ
                     ባለሙያ ወይም የፖለቲካ ድርጅት ከሚዘጋጁ ይልቅ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ
                     በሆኑ  የፖለቲካ  ፓርቲዎች  የተወከሉ  ግለሰቦች  በጋራ  እንዲያዘጋጁ  እና
                     እንዲያቀርቡ  ማድረግ  ነው።  ይህም፣  የተለያየ  አመለካከት  ባላቸው  ወገኖች
                     ሊኖር የሚገባውን የመደማመጥ እና የመተባበር ባህል ያዳብራል።
               xv.   የመወያያ ጽሁፎቹ ከቀረቡ እና በጽሁፎቹ ላይ ለሚነሱ የማብራሪያ ጥያቄዎች
                     መልስ ክተሰጡ በኋላ የምልዐተ ስብሰባ እና የቡድኖች ውይይት ቅይጥ አካሄድ
                     መከተል  ሃሳቦች  በደንብ  የሚብላሉበትን  ሁኔታ  ከመፍጠሩም  ባሻገር
                     በተሳታፊዎቹ  መካከል  ሊፈጠር  የሚገባውን  ግለሰባዊም  ሆነ  ቡድናዊ
                     መስተጋብር ይበልጥ ስኬታማ እና ጤናማ እየሆነ እንዲሄድ ያደርገዋል።
              xvi.   ከዚህ  በላይ  ከተጠቀሱት  የአካሄድ  መርሆች  ባሻገር፣  እንዲህ  ዓይነት  ጉባዔ
                     ውጤታማ  እንዲሆን  ከተፈለገ፣  ሁሉም  ተሳታፊዎች  በተናጠልም  ሆነ  በጋራ
                     ሊያከብሯቸው የሚገቡ መሰረታዊ የሥነምግባር መመሪያዎች መካከል ዋነኛው
                     ሁሉም  ተሳታፊዎች  ለሀገራቸው  እድገት  እና  ለህዝባቸው  ኑሮ  መሻሻል  ቀና
                     አስተሳሰብ  ይዘው  የተነሱ  ናቸው  የሚል  ግምት  (benefit  of  the  doubt)
                     መስጠት ነው።
              xvii.   ከዚህ በተጨማሪ፣ በእንዲህ አይነት መድረክ የሚቀርቡ ማናቸውንም ሃሳቦች
                     በሃሳብ መሞገት እንጂ ለምን እንዲህ ተባለ ብሎ ፖለቲካዊ ፍረጃ እና ቅጥያ
                     (Political  labelling)  ለመስጠት  አለመሞከር፤  እና  ለብሔራዊ  መግባባት
                     የሚደረግ ውይይት ዘላቂ፣ ሃገራዊ እና ህዝባዊ ሰላም እና ልማት ለማረጋገጥ
                     የሚደረግ  ውይይት  እንጂ  ለምርጫ  መፎካከሪያ  የሚሆን  የፖለቲካ  ነጥብ
                     ማስቆጠሪያ እንዳልሆነ መተማመን ነው።











                                                                        91
   94   95   96   97   98   99   100   101   102   103   104