Page 94 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 94
ደስታ መብራቱ
ከላይ እንደተጠቀሰው፣ ባሁኑ ስዓት በተለያየ ደረጃ እየተካሄደ ያለው የብሔራዊ
መግባባት ውይይት በቅርብ ጊዜው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው
መልካም አጋጣሚ ነው ማለት ይቻላል። ይህንን አጋጣሚ ውጤታማ ለማድረግ ቁልፉ
መለኪያ አጠቃላይ ሂደቱ ትብብራዊ አስተሳሰብን (collaborative thinking)
በሚያጠናክር መልኩ እንዲዋቀር ማድረጉ ላይ ነው። የሚፈለገውን የአስተሳሰብ ሽግግር
ለማምጣት እና ወደ መፍትሔዎቹ ለማምራት የምህዳራዊ አስተሳሰብ ዋና ዋና መርሆዎችን
መሰረት በማድረግ ሶስት ምዕራፍ ባለው ትብብራዊ የአስተሳሰብ (Collaborative
thinking) ሂደት ውስጥ ማለፍን ይጠይቃል። የመጀመሪያው፣ በሀገሪቱ መሰረታዊ
የፖለቲካ ጥያቄዎች ላይ የሚነሱ የተለያዩ ሃሳቦች እና አቋሞች የሚጠበቁ መሆኑን
ተገንዝቦ፣ ምንም ያህል የተቃረኑ (divergent) ቢመስሉም፣ ከልብ ለመስማት እና
ለመደማመጥ የሚያስችል ዝግጁነት መፍጠር እና ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነው።
ምስል ሶስት፡ ትብብራዊ የአስተሳሰብ ሂደት (Collaborative thinking
process)
ከዚህ በመቀጠል፣ ለተቃራኒ አመለካከቶች መነሻ የሆኑ ተጨባጭ እና ግምታዊ
ስጋቶችን ለመረዳት መጣር ያስፈልጋል። ይህን ለማድረግም፣ ሌሎች ወገኖች የሚያነሷቸውን
ጥያቄዎች እና ሃሳቦች ተገቢውን አክብሮት መስጠት እና ሥረ-መሰረቱን በእነርሱ ቦታ ሆኖ
ለመረዳት መሞከርን ይጠይቃል። ከዚህ በተጨማሪ፣ በተገኘው የሃሳብ መግባባት ላይ
በመመርኮዝ ያሉትን ስጋቶች እና ቅሬታዎች ሲቻል ለመፈወስ ይህም ባይቻል ድጋሚ
እንዳይከሰቱ ለማድረግ የሚያስችል አዲስ እይታ እንዲመነጭ (emergence) ማድረግ