Page 93 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 93
ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ
በዚህም መሰረት፣ የሂደቱ ተሳታፊዎች በሃገራችን ፖለቲካ ውስጥ ያሉትን
መዋቅራዊ አይገመቴዎች (structural uncertainties) በሚገባ መለየት ችለው ነበር።
ከምህዳራዊ አስተሳሰብ አኳያ፣ መዋቅራዊ አይገመቴዎችን ከለዩ በኋላ መሰረታዊ
ምንጮቻቸውን መረዳት እና እነርሱም የሚያስከትሉትን የተለያዩ እንደምታዎች መተንተን
ወደ አሻጋሪ ቢሆንሶቹ የሚወስድ መሰረታዊ ሂደት ነው። የምንፈልጋት ኢትዮጵያ ሂደት
ይህንን መሰረታዊ የትንተና ደረጃ በመዝለል ከመዋቅራዊ አይገመቴዎች በቀጥታ
ቢሆንሶቹን ወደ መግለጽ ውስጥ ገብቷል። የዚህም ውጤት በአብዛኛው ህብረተሰብ
ሊገመቱ የሚችሉ አንድ የተስፋ እና ሶስት የስጋት ቢሆንሶችን ከማውጣት ሊዘል
አልቻለም።
እዚህ ላይ፣ ይህንን ሂደት ከሃሳብ ማመንጨት እስከ መጨረሻው ተግባራዊነት
የነበረውን አድካሚ ስራ በማስተባበር የመሩት ኢትዮጵያዊያን እና በሂደቱ ውስጥ ንቁ
ተሳትፎ ያደረጉት የምንፈልጋት ኢትዮጵያ ቡድን አባላት አድናቆት ሊቸራቸው ይገባል።
ይህ ሂደት ለሃገሪቱ የፖለቲካ ችግሮች መፍትሄ ለመሻት ያደረገው አስተዋጽኦ ቢኖርም፣
34
በሂደቱ የመጨረሻ ክፍል የታየው መሰረታዊ ያካሄድ ግድፈት በተገኘው የመግባባት
መንፈስ ላይ በመገንባት ለሃገሪቱ የፖለቲካ ችግር አመላካች የሆኑ መፍትሄዎችን
ለማመንጨት የሚያስችለውን እድል እንዲያመልጠው አድርጎታል።
አሁንም ሆነ ወደፊት ሊካሄዱ የሚችሉ የብሔራዊ መግባባት ውይይቶች
ከምንፈልጋት ኢትዮጵያ ሂደት ሊማሩ የሚችላቸው በርካታ ቁምነገሮች ሲኖሩ፣
የሚከተሉትን በዓበይትነት መጥቀስ ይቻላል። የመጀመሪያው፣ ምንም እንኳን በአሁኑ ሰዓት
በሃገሪቱ የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች እጅግ የተለያየ አንዳንዴም የማይታረቅ የሚመስል
አቋም ያላቸው ቢመስልም በጽሞና ለመደማመጥ በሚያስችል ሁኔታ ከተወያዩ መግባባት
የሚችሉበት አጋጣሚ ከፍተኛ መሆኑን ነው። ሁለተኛው፤ የብሔራዊ መግባባት ውይይቱ
የተሳካ እንዲሆን የሃገሪቱን ውስብስብ ሁኔታ በሚመጥን እና በብዙ መሰል ውስብስብ
ሂደቶች ላይ በተፈተነው የዓይነታዊ ለውጥ አስተሳሰብ (transformational thinking)
ዘዴ እና ዕውቀት ሊደገፍ ይገባል። ይህንን ዐውቀት ለመሻትም ባህር አቋርጦ ወደ ውጭ
መመልከት የሚያስፈልግ ሳይሆን በሃገራችን የሚገኙ ሃገር በቀል የውይይት እና መደማመጥ
ሥርዓቶችን፣ ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት ከሚያስችሉ የዘመኑ ዕውቀት እና ዘዴዎች ጋር
በማሰናሰል መጠቀም ይቻላል። ይህንን መሰረት በማድረግ፣ ከምህዳራዊ አስተሳሰብ አኳያ
በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደ ያለውን እና ወደፊትም የሚካሄደውን የብሔራዊ መግባባት
ውይይት ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ አንዳንድ መሰረታዊ ነጥቦችን ከዚህ በመቀጠል
ተመልክተዋል።
34 የዚህ ግድፈት ዋነኛው ምክንያት፣ ለዚህ ሂደት በዓለም አቀፍ አማካሪነት የተመረጠው ቡድን
በምህዳራዊ አስተሳሰብ ላይ ስለተመረኮዙ ዓይነታዊ የለውጥ ቢህንሶች (Transformational
scenrios) ያለው ዕውቀት ውሱን መሆን ነበረ።
85