Page 96 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 96

ደስታ መብራቱ


                  ከትብብራዊ አስተሳሰብ አኳያ ተመራጩ መንገድ፣ ባንድ ርዕስ ላይ የሚቀርብን
           የመወያያ ጽሁፍ ከሶስት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወከሉ ግለሰቦች
           በጋራ  እንዲያዘጋጁ  እና  እንዲያቀርቡ  ማድረግ  ነው።  በዚህ  ሂደት  ውስጥ፣  አዘጋጆቹ
           የሚጠበቅባቸው በተሰጣቸው ርዕስ ላይ የሚግባቡባቸውን እና የሚለያዩባቸውን አንኳር
           ነጥቦች  ለይተው  በማቅረብ  በሚግባቡባቸው  ነጥቦች  ላይ  እንዴት  አብሮ  መስራት
           እንደሚቻል እና የሚለያዩባቸውን ነጥቦች እንዴት ሊስተናገዱ እንደሚችሉ ማመላከት
           ይሆናል። ይህንን አካሄድ በመጠቀምም፣ የጋራ ሃላፊነት በተሰጣቸው ግለሰቦች መካከል
           የተሻለ የሃሳብ ግንኙነት እና መረዳት ከመፍጠር ባሻገር ለብሔራዊ መግባባት መፈጠር
           የሚያግዙ መሰረታዊ ጡቦችን (building blocks) ደረጃ በደረጃ ለማስቀመጥ የሚያስችል
           ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋል።
                  ከርዕስ መረጣ እና የመወያያ ጽሁፍ አዘገጃጀት ባልተናነሰ ቁልፍ ድርሻ ያለው
           ሶስተኛው አካሄድ፣ በጽሁፎቹ ላይ የሚካሄዱ ውይይቶች አደረጃጀት ይሆናል። በሚድያ
           ሲተላለፍ እንደታየው ከሆነ፣ እስካሁን በተደረጉት ስብሰባዎች ላይ ጽሁፎቹ ከቀረቡ በኋላ
           ሁሉም ተሳታፊዎች ባሉበት ምልዐተ ስብሰባ (plenary) ላይ ውይይቱ ይቀጥላል። እንዲህ
           አይነቱ  አካሄድ፣  ሃሳባቸውን  ለማካፈል  የሚፈልጉ  ተሳታፊዎች  የሚኖራቸውን  እድል
           የሚያጠብ ከመሆኑም በላይ  በዋነኛ  ነጥቦች  ላይ ትኩረት  ያደረገ  እና ውጤታማ የሆነ
           ውይይት ለማካሄድ የሚኖረውን እድል እጅግ ፈታኝ ያደርገዋል። ከዚህ ይልቅ ተመራጩ
           እና  ውጤታማው  መንገድ፣  የመወያያ  ጽሁፎቹ  ከቀረቡ  እና  በጽሁፎቹ  ላይ  ለሚነሱ
           የማብራሪያ  ጥያቄዎች  መልስ  ክተሰጡ  በኋላ  ያሉትን  ተሳታፊዎች  በአነስተኛ  ቡድኖች
           በመከፋፈል በቀረቡት ጽሁፎች ላይ ተወያይተው የሚደርሱበትን ማጠቃለያ ለምልዐተ
           ስብሰባው ለውይይት እንዲያቀርቡ ማድረግ ነው።
                  እንዲህ ዓይነቱ የምልዐተ ስብሰባ እና የቡድኖች ውይይት ቅይጥ አካሄድ ሃሳቦች
           በደንብ  የሚብላሉበትን  ሁኔታ  ከመፍጠሩም  ባሻገር  በተሳታፊዎቹ  መካከል  ሊፈጠር
           የሚገባውን ግለሰባዊም ሆነ ቡድናዊ መስተጋብር ይበልጥ ስኬታማ እና ጤናማ እየሆነ
           እንዲሄድ  ያደርገዋል።  ይህም፣  ፓርቲዎቹ  ይበልጥ  እየተሰባሰቡ  እንዲሄዱ  ሊያግዛቸው
           ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ፣ የብዙ መሰል ጉባኤዎች ልምድ እንደሚያመላክተው፣ እንዲህ
           አይነት  ስብሰባዎች  ላይ  ቢያንስ  በቡድን  ተከፋፍለው  የሚደረጉ  ውይይቶችን  ከሚድያ
           እይታ  ውጭ  እንዲካሄዱ  ማድረግ  ይመከራል።  ይህም፣  ተሳታፊዎች  በፍጹም  ነጻነት
           ሃሳባቸውን  እንዲገልጹ  ከማበረታታቱም  ባሻገር  በደንብ  ያልተብላሉ  ሃሳቦችን  በሚዲያ
           በማሰራጨት ሊፈጠሩ ከሚችሉ ብዥታዎች ህብረተሰቡን መጠበቅ ያስችላል።
                  ከዚህ  በላይ  ከተጠቀሱት  የአካሄድ  መርሆች  ባሻገር፣  እንዲህ  ዓይነት  ጉባዔ
           ውጤታማ እንዲሆን ከተፈለገ፣ ሁሉም ተሳታፊዎች በተናጠልም ሆነ በጋራ ሊያከብሯቸው
           የሚገቡ መሰረታዊ የሥነምግባር መመሪያዎች ይኖራሉ። ከዚህ ውስጥ የመጀመሪያው እና
           ዋነኛው  ሁሉም  ተሳታፊዎች  ለሀገራቸው  እድገት  እና  ለህዝባቸው  ኑሮ  መሻሻል  ቀና
           አስተሳሰብ ይዘው የተነሱ ናቸው የሚል ቀና ግምት (benefit of the doubt) መስጠት
           ይሆናል።  እንዲህ  አይነቱ  እምነት፣  በህዝቦች  ዳኝነት  ከማመን  ጋር  በጥብቅ  የተሳሰረ
   91   92   93   94   95   96   97   98   99   100   101