Page 97 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 97

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


             በመሆኑ  ፖለቲከኞቻችን  የየትኛውንም  የፖለቲካ  ድርጅት  ወይንም  ፖለቲከኛ
             የመጨረሻውን ዳኝነት በነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ለሚወስነው ህዝብ ሊተዉለት ይገባል።

                     ከዚህ በተጨማሪ፣ በእንዲህ አይነት መድረክ የሚቀርቡ ማናቸውንም ሃሳቦች
             በሃሳብ  መሞገት  እንጂ  ለምን  እንዲህ  ተባለ  ብሎ፣  ከዚህ  በፊት  በተካሄዱ  አንዳንድ
             ውይይቶች ላይ እንደታየው፣ ፖለቲካዊ ፍረጃ እና ቅጥያ (Political labelling) ለመስጠት
             መሞከር አይገባም። ይህ ፖለቲካዊ ቅጥያ የመስጠት ዝንባሌ ከተማሪው እንቅስቃሴ ጀምሮ
             ፖለቲካችንን  የተጠናወተ  በሽታ  በመሆኑ  በዚህ  ዘመን  ልናስወግደው  ይገባል።  ከዚህ
             በተጨማሪ፣ ለብሔራዊ መግባባት የሚደረግ ውይይት ዘላቂ፣ ሃገራዊ እና ህዝባዊ ሰላም
             እና ልማት ለማረጋገጥ የሚደረግ ውይይት እንጂ ለምርጫ መፎካከሪያ የሚሆን የፖለቲካ
             ነጥብ  ማስቆጠሪያ  እንዳልሆነ  ሁሉም  ተሳታፊዎች  ሊገነዘቡት  ይገባል።  በመጨረሻም
             የአህጉራችን ታላቅ ሰው የሆኑት ኔልሰን ማንዴላ እንደተናገሩት ውስብስብ የፖለቲካ ፈተና
             ውስጥ ለሚገኙ ሃገራት ብሔራዊ መግባባት፣ ተግባራዊ ሆኖ እስከሚገኝ ድረስ በጭራሽ
             የማይቻል መስሎ ይታያል። ነገር ግን ይቻላል፤ ተችሏልም።
             የክፍል ስድስት ቁልፍ ሐሳቦች
                i.   በማናቸውም ማህበረሰብ ወይም ሃገር ውስጥ የተለያዩ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ
                     እና  የልማት  ተረኮች  መኖር  የሚጠበቅ  ሲሆን  እነኚህ  ተረኮች  ግን  ለተለያዩ
                     ግጭቶች መነሻ የሚሆኑት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በማደግ ላይ ባሉ ሃገሮች ውስጥ
                     ብቻ  ነው።  የዚህም  ዋነኛው  ምክንያት፣  በተለያዩ  ተረኮች  መካከል  የሚኖሩ
                     አለመጣጣሞችን  ሲቻል  ለማስታረቅ  ያም  ካልተቻለ  ደግሞ  ለመዳኘት
                     የሚያስችሉ ተቋማዊ አደረጃጀቶች እና ሥርዓቶች ደካማ ሆነው መገኘታቸው
                     ነው።
                ii.   በእንዲህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሃገሮች ለወደፊት እጣ ፈንታቸው ወሳኝ
                     ከሆኑ የሽግግር ወቅት ጋር በሚፋጠጡበት ጊዜ የብሔራዊ መግባባት ውይይት
                     ማካሄድን  እንደ  አንድ  ዓብይ  መፍትሔ  ይጠቀሙበታል።  ለዚህም  መሳካት
                     የመጀመሪያው አስፈላጊ ነጥብ፣ በማህበራዊ ተረክ እና በተቋማዊ ተረክ መካከል
                     ያለውን አይነታዊ ልዩነት መረዳት ነው።
               iii.   ማህበረሰባዊ  ተረክ  (social  narrative)፣  አንድ  ማህበረሰባዊ  ቡድን
                     የመጣበትን፣  ያለበትን  እና  የሚሄድበትን  ማህበራዊ  ፍኖት  የሚረዳበት  እና
                     የሚገልጽበት (collective sensemaking) ሲሆን የዚያን ማህበረሰብ አባላት
                     የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በመወሰን ረገድ ታላቅ ጉልበት አለው።
               iv.   በንግግር እና በተግባር ካሉት መገለጫዎች ባሻገር፣ ማንኛውም ማህበረሰባዊ
                     ተረክ  የዚያ  ማህበረሰብ  የእምነት  ስርዓቶች  እና  ዕሴቶች  (value  systems)
                     ምናባዊ  ማከማቻም  ነው።  ስለሆነም  አንድን  ማህበረሰባዊ  ተረክ  ባግባቡ
                     ለመረዳት  የዚያን  ማህበረሰብ  የዕሴት  መስረቶችን  በጥልቅ  መመርመር  እና
                     መረዳት ያስፈልጋል።

                                                                        89
   92   93   94   95   96   97   98   99   100   101   102