Page 102 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 102

ደስታ መብራቱ


           እንደሚያደርግባቸው  ይጠበቃል።  በመሆኑም፣  እንደ  ኢትዮጵያ  ያሉ  ሃገሮች
           የሚያወጧቸው  ብሔራዊም  ሆነ  የዘርፍ  የልማት  ፖሊሲዎች  የአየር  ንብረት  ለውጥ
           ተጽእኖን መቋቋም የሚችል (climate resilient) እድገት ለማምጣት በሚያስችል መንገድ
           መቅረጽ እና መተግበራቸው አካታች እና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ በጣም አስፈላጊ ነው።

                  የተፈጥሮ ሃብት መመናመን (Natural resource depletion)፡ በዓለም አቀፍ
           የሳይንቲስቶች የተፈጥሮ ሃብት ጥናት ቡድን (International Respurce Panel) መሰረት፣
           በሃያኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ብቻ ከተፈጥሮ አካባቢያችን የወሰድነው አጠቃላይ የተፈጥሮ
           ሃብት በስምንት እጥፍ ሲያድግ፣ እ.ኤ.አ. በ1900 ሰባት ቢሊዮን ቶን የነበረው በ2010 ወደ
           60 ቢሊዮን ቶን አድጓል። እስከዛሬ በመጣንበት መንገድ ከቀጠልን፣ እ.አ.አ. በ2050 አንድ
           መቶ አርባ ቢሊዮን ቶን እንደሚደርስ ይገመታል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በደረሰው የተፈጥሮ
           ሃብት  መመናመን  የተነሳ፣  ከ1970  እስክ  2010  በነበሩት  አርባ  ዓመታት  ውስጥ  ብቻ
           የዓለማችን  የብዝሃ  ህይወት  መለኪያ  (Living  planet  index)  በሃምሳ  ሁለት  በመቶ
           ቀንሷል። ይህ ከዚህ በላይ የተጠቀሰው የተፈጥሮ ሃብት መመናመን፣ የምድራችን ውሃን
           ጨምሮ፣  እያደገ  የሚሄደውን  የዓለም  ህዝብ  የተፈጥሮ  ሃብት  ፍላጎት  ማሟላት  ወደ
           ማይችልበት ደረጃ አድርሷታል። ከዚህ በተጨማሪ፣ ይኽው የተፈጥሮ ሃብት መመናመን
           ባሁኑ ሰዓት ዓለማችንን ከዳር እስከዳር ያንበረከከው የኮሮና ወረርሽኝ ከእንስሳት ወደ ሰው
           የሚተላፍበትን ሁኔታም አመቻችቷል።
                  ሁኔታዎች በመሰረታዊነት ካልተቀየሩ፣ እንዲህ አይነቱ አደጋ በመጪዎቹ ዐስርተ
           ዓመታት እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል ተገምቷል። የተፈጥሮ ሃብት መመናመንም ሆነ
           የወረርሽኝ በሽታዎች መከሰት እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በማደግ ላይ ላሉ እና ከፍተኛ የህዝብ
           ቁጥር  እድገት  ለሚታይባቸው  ሃገሮች  በጣም  ፈታኝ  እንደሚሆንባቸው  ይጠበቃል።
           የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ባወጣው  የ2020 የሰብዓዊ ልማት ዕድገት
           ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ ባሁኑ ወቅት አላት ተብሎ ከሚገመተው ታዳሽ የተፈጥሮ ሃብት
           አቅም (bio-capacity) 99.7% በመጠቀም ላይ ትገኛለች። ይህ የሚያመላክተው የሃገሪቱ
           የተፈጥሮ  ሃብት  አጠቃላይ  የመሸከም  አቅምን  (carrying  capacity)  ሙሉ  ለሙሉ
           በመጠቀማችን፣  ተጨማሪ  ጫና  ለማስተናገድ  ያለን  ቀሪ  አቅም  ዜሮ  መሆኑን  ነው።
           ስለዚህም፣ ሃገሪቱ የምትተገብራቸው የልማት እቅዶች በሙሉ፣ የሃገሪቱን የተፈጥሮ ሃብት
           መሰረት  (ecological  foundation)  ይበልጥ  የሚያጠናክሩ፣  ምርታማ  የሆነ  የተፈጥሮ
           ሃብት አጠቃቀምን (resource efficiency) የሚያረጋግጡ፣ እና የሃገሪቱን ብዝሐ ህይወት
           የሚያበራክቱ ሊሆኑ ይገባል።
                     የህዝብ ብዛት ጫና (Population pressure): በህዝብ ብዛት እና በተፈጥሮ
           አካባቢ መካከል ያለው ያልተቋረጠ መስተጋብር ዓለማችን ዛሬ ያለውን ገጽታ እንዲይዝ
           በማደረጉ በኩል ከፍተኛውን አስተዋጽኦ እንዳደረገ ይታመናል። ይህም፣ ሁለት አበይት
           ምዕራፎችን የያዘ ነው። የመጀመሪያው፣ በርካታ ሺዎች ዓመታትን የሚሸፍነው የቅድመ
           ታሪክ   ዘመን  ሲሆን  የዚህም  ዋነኛው  መለያ  በአንድ  አካባቢ  ያለው  የተፈጥሮ  ሃብት
           ሲመናመን ወደ አልተነካ ለም አካባቢ (green pasture) መነቃነቅ ነው። ይህ ከተራቆተ
   97   98   99   100   101   102   103   104   105   106   107