Page 105 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 105
ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ
7.2 ብሔራዊ ፈተናዎቻችን እና መፍትሄዎቻቸው
ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ዓለም አቀፋዊ ቅርጽ እና ይዘት ካላቸው ፈተናዎች
በተጨማሪ፣ ከሀገራዊው ልዩ ሁኔታዎች ጋር የሚያያዙ ፈተናዎች አሉ። እነኚህን ፈተናዎች
በአግባቡ ለይቶ መረዳት እና መፍትሄ መሻት ከዓለም አቀፋዊው ፈተናዎች ሊደርሱ
የሚችሉ ተጽአኖዎችን ለመቋቋምም ሆነ ወደ አካታች እና ዘላቂ ልማት የሚደረገውን
ግስጋሴ ለማፋጠን አቢይ ድርሻ ይኖረዋል። በዚህ ረገድ ሊነሱ ከሚችሉ በርካታ ፈተናዎች
እና መፍትሄዎቻቸው መካከል የሚከተሉትን በአበይትነት መጥቀስ ይቻላል።
የሁለንተናዊ ደህንነት ኢኮኖሚ (Wellbeing Economy) ፖሊሲ፡ አትዮጵያን
ጨምሮ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሃገሮች ባላፉት በርካታ ዐስርተ ዓመታት የተገበሯቸው
የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች በተሳሳቱ (misguided) ቅኝቶች ላይ የተመረኮዙ በመሆናቸው
የህዝቦቻቸውን ኑሮ ከዕለት ወደ ዕለት ለባሰ ድህነት እና ጉስቁልና እያጋለጡ በመሄድ ላይ
ይገኛሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ ከነበረው የኢኮኖሚም ሆነ የፖለቲካ የኃይል አሰላላፍ አኳያ
የእነኚህ ሃገሮች ፖሊሲዎች በምዕራባውያን ሃገሮች ሲራመድ በነበረው የነጻ ገበያ
የኢኮኖሚ ሥርዓት እና በሶሻሊስቱ ዓለም በተራመደው የተማከለ የኢኮኖሚ ሥርዓት
መሃል መዋዠቁ ብዙም የሚያስገርም ላይሆን ይችላል። ትልቁ ችግር የሚመነጨው
የቀረበላቸውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ አማራጭ ከሃገራዊው ልዩ ፍላጎት እና ጥቅም ጋር
ሳያጣጥሙ በጅምላ ወስደው ለመተግበር መሞከራቸው ነው።
ከዚህ በተጨማሪም፣ የፖሊሲ አማራጮቹ የሚመዘኑበት ዋነኛው መለኪያ
የህዝቦችን የኑሮ ሁለንተናዊ ደህንነት (wellbeing) ለማሻሻል በሚኖራቸው አስተዋጽኦ
ሳይሆን በስልጣን ላይ ላለው ቡድን ፖለቲካዊ ዓላማዎች መሳካት በሚያበረክቱት ድርሻ
መሆኑ ነው። በዚህም የተነሳ፣ በአንድ ታዋቂ ፓን አፍሪካዊ ምሁር እንደተባለው፣ ብዙዎቹ
የአፍሪካ ሃገሮች የሚያራምዷቸው የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች በምትሃታዊ የኢኮኖሚ ፍልስፍና
35
(Voodoo economics) የተቃኙ አስመስሏቸዋል ። ከዚህ አይነት አዙሪት ለመውጣት፣
እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሃገሮች የህዝቦችን መስረታዊ የኑሮ ዋስትና የሚያረጋግጡ እና ሃገራዊ
ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የሁለንተናዊ ደህንነት ኢኮኖሚ (Wellebing economy)
ፖሊሲዎችን ለመቅረጽና ለመተግበር መጣር ይኖርባቸዋል። የዚህም አንዱ እና ዋነኛው
መገለጫ፣ ከውጭ ቀጥተኛ መዋዕለ ንዋይ (Foreign direct investment) በበለጠ፣
ሀገራዊውን የተፈጥሮ ሃብት (natural resource) እና የሰው ኃይል (human capital)
እንደ ዋነኛው የአካታች እና ዘላቂ ልማት አንቀሳቃሽ አድርጎ መውሰድ እና ይህንን በዘመኑ
የዕውቀት እና የቴክኖሎጂ ግብአቶች ማበልፀግ እና ጥቅም ላይ ማዋል ነው።
35 በዚህ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት https://teifaiq.com/2020/09/07/from-voodoo-
economics-to-a-well-being-economy-africas-choice/ ይጎብኙ።
97