Page 111 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 111

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


             ሊሆን እንደሚችል ይታመናል። ለዚህም፣ ወጣቱን ትውልድ ዘመኑ ከሚፈጥረው ዕውቀት
             እና ቴክኖሎጂ ጋር ከመደበኛው ትምህርቱ ጎን ለጎን አንዲተዋወቅ ማድረግ እና የመፍትሔ
             ፈጣሪነት ክህሎቱን ማዳበር ያስፈልጋል። ይህንን በማድረግ፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በማደግ
             ላይ ያሉ ሃገሮች ከፈጣን የህዝብ ብዛት እድገት ጋር ሊመጣ የሚችለውን ፈተና ከፍተኛ
             ትሩፋት ሊፈጥሩ ወደሚችሉ እድሎች መቀየር ይችላሉ።

                     ዓይነታዊ  የለውጥ  መሠረተ  ልማት  (Transformational  infrastructure)፡
             የአፍሪካ ሃገሮች ኢኮኖሚ ላይ የተካሄዱ በርካታ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት፣ በአብዛኞቹ
             የአፍሪካ ሃገሮች ውስጥ ጎልቶ የሚታየው የመሠረተ ልማት ክፍተት ለብዙዎቹ የኢኮኖሚ
             ዕድገት ደካማነት ዋነኛ ምክንያት ነው። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ባላፉት ጥቂት ዓስርተ
             ዓመታት እጅግ ፈጣን በሆነ ሁኔታ እየበለፀገ ከመጣው የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታ
             ዕውቀት እና ቴክኖሎጂ አኳያ ሲታይ፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሃገሮች ወደ ኋላ መቅረት እንደ
             መልካም  አጋጣሚ  ተደርጎ  ሊወሰድ  ይችላል።  ምክንያቱም  እነኚህ  ሃገሮች
             የሚያስፈልጓቸውን ማናቸውም መሠረተ ልማቶች ልማዳዊ (conventional) በሆነው እና
             ሃብት አባካኝ እና ኢዘላቂ (unsustainable) በሆነ የግንባታ መንገድ ከማልማት ይልቅ፣
             የረጂም ዘመን አዋጪነታቸው እና ዘላቂነታቸው በተረጋገጠ እውቀት እና ቴክኖሎጂ  ላይ
             በመገንባት አካታች እና ዘላቂ ልማትን ማሳካት ይችላሉ።

                     ይህንን  ተግባራዊ  ለማድረግ  ከሚያስችሉ  የዕውቀት  መሳሪያዎች  አንዱ  እና
             ዋነኛው የማንኛውንም መሠረተ ልማት ሙሉ የህልውና ዑደት የሚሸፍን እቅድ አወጣጥ
             እና ሥራ አመራር (life-cycle management) መርህን መተግበር ይሆናል። ዓይነታዊ
             የለውጥ መስረተ ልማት ግንባታ፣ ሃገሮች በመሰረተ ልማት ላይ ከሚያውሉት መዋዕለ
             ንዋይ ማግኘት የሚገባቸውን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ጥቅም ከማረጋገጡም በላይ የልማቱን
             አካታችነትም  ያረጋግጣል።  በተለያዩ  ጥናቶች  እና  በተግባርም  እንደተረጋገጠው፣
             ማንኛውም  የመሰረተ  ልማት  ከዕቅድ  ነደፋው  ጀምሮ  አስከ  ግንባታው  ፍፃሜ  ድረስ
             የሚጠቀመው  ዘዴ  መሰረተ  ልማቱ  ተግባር  ላይ  ሲውል  የሚኖረውን  አካታችነትም
             ይወስነዋል።  ከዚህም  በተጨማሪ፣  ዓይነታዊ  የመሰረተ  ልማት  ግንባታ  መርሆዎችን
             መከተል  እንደ  ኢትዮጵያ  ያሉ  ሃገሮች  የሚኖርዋቸውን  በኪሳራ  የታጠሩ  ንብረቶች
             (stranded assets) ቁጥር ለመቀነስ ያስችላቸዋል።










                                                                       103
   106   107   108   109   110   111   112   113   114   115   116