Page 115 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 115

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


               xx.   ኢትዮጵያ ሃገራችን በዓለም ውስጥ ከሚገኙ በጣም ጥቂት ከፍተኛ የተፈጥሮአዊ
                     ምህዳር፣ የእንስሳት እና የዕፅዋት ሃብት ብዝሃነት ከሚታይባቸው ሃገሮች ውስጥ
                     ትመደባለች።  እንዲህ  ዓይነቱ  ዘርፈ  ብዙ  የሆነ  የብዝሃነት  ሃብት  የሃገሪቱ
                     የተፈጥሮ ሃብት መሰረት ከፍተኛ የማገገም አቅም (resilience) እንዲኖረው
                     ያደርገዋል።
              xxi.   ስለዚህም፣ የማናቸውም የልማት ፍላጎታችን መሟላት ዋነኛ መሰረት የሆነውን
                     የተፈጥሮ  አካባቢያችንን  መንከባከብ  እና  ማልማት  ከህጻንነት  ጀምሮ
                     የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ባህል እንዲሆን ማድረግ የሁሉንም ተጠቃሚነት
                     የሚያረጋግጥ አካታች እና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ ዋነኛው ዋስትናችን ነው።
              xxii.   ኢትዮጵያን ጨምሮ፣ ያብዛኞቹ የአፍሪካ ሃገሮች ፈተና ከምዕራባዊው ዓለም
                     የሚጫንባቸውን  ማንኛቸውም  አስተሳሰቦች፣  ልማዶች፣  እና  ቴክኖሎጂዎችን
                     ያለአንዳች ሃገራዊ ምልከታ እና ለውጥ (adaptation) እንዳሉ መቀበላቸው እና
                     ለመጠቀም  መሞከራቸው  ነው።  በአራተኛው  የኢንዱስትሪ  አብዮት  ዘመን
                     የተዛቡ  የቴክኖሎጂ  መረጣ  እና  ሽግግር  ውሳኔዎች  ከፍተኛ  ዋጋ
                     ከማስከፈላቸውም በላይ የሃገሪቱን ዘላቂ ልማት እድሎች ሊያጠቡ ይችላሉ።
              xxiii.   ይህን  መሰል  አደጋዎች  ለመቀነስ  እና  ለማስወገድ፣  ወደእኛ  የሚጎርፉ
                     ማንኛውንም  የቴክኖሎጂ  ውጤቶችን  በዕውቀት  ላይ  በተመረኮዘ  የዓይነታዊ
                     እመርታ መርሆዎች መስረት ማንኛውንም ቴክኖሎጂን ለሃገሪቱ ልዩ ሁኔታ እና
                     ዘላቂ ልማት ግቦች በሚስማማ መልኩ በትኖ መፈተሽ (unpack) እና አስማምቶ
                     ስራ ላይ ማዋል ያስፈልጋል።
              xxiv.   ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ በማደግ ላይ የሚገኙ ሃገሮች በከፍተኛ የህዝብ
                     ብዛት  እድገት  የመፈተናቸውን  ያክል፣  ልዩ  ትሩፋት  ሊሰጣቸው  የሚያስችል
                     እድልም  አላቸው።  የዚህም  ዋነኛ  ምክንያት፣  ካደጉት  ሃገሮች  በተቃራኒው፣
                     የህዝባቸው አብዛኛው ክፍል አምራች በሆነው የእድሜ ክልል ውስጥ መገኘቱ
                     ነው። ይህንን ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ወጣት እና አምራች የህብረተሰብ ክፍል
                     በአግባቡ በማበልፀግ ወደ ምርታማ የሰው ሃይልነት መቀየር ከተቻለ ሃገሪቱን
                     ወደ  ከፍተኛ  እድገት  ለማሸጋገር  ታላቅ  አጋዥ  ኃይል  ሊሆን  እንደሚችል
                     ይታመናል።
              xxv.   ባላፉት ጥቂት ዓስርተ ዓመታት እጅግ ፈጣን በሆነ ሁኔታ እየበለፀገ ከመጣው
                     የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታ ዕውቀት እና ቴክኖሎጂ አኳያ ሲታይ፣ እንደ
                     ኢትዮጵያ  ያሉ  ሃገሮች  ወደ  ኋላ  መቅረት  እንደ  መልካም  አጋጣሚ  ተደርጎ
                     ሊወሰድ ይችላል። ምክንያቱም እነኚህ ሃገሮች የሚያስፈልጓቸውን ማናቸውም
                     መሠረተ ልማቶች ልማዳዊ (conventional) በሆነው እና ሃብት አባካኝ እና
                     ኢዘላቂ (unsustainable) በሆነ የግንባታ መንገድ ከማልማት ይልቅ፣ የረጂም
                     ዘመን አዋጪነታቸው እና ዘላቂነታቸው በተረጋገጠ ቴክኖሎጂ  ላይ በመገንባት
                     አካታች እና ዘላቂ ልማትን ማሳካት ይችላሉ።


                                                                       107
   110   111   112   113   114   115   116   117   118   119   120