Page 116 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 116

ደስታ መብራቱ


           xxvi.   ዓይነታዊ  የለውጥ  መስረተ  ልማት  ግንባታ፣  ሃገሮች  በመሰረተ  ልማት  ላይ
                  ከሚያውሉት  መዋዕለ  ንዋይ  ማግኘት  የሚገባቸውን  ሁለንተናዊ  የኢኮኖሚ
                  ጥቅም ከማረጋገጡም በላይ የልማቱን አካታችነት በማረጋገጥ ረገድም ከፍተኛ
                  አስተዋጽኦ  ይኖረዋል።  በተለያዩ  ጥናቶች  እና  በተግባርም  እንደተረጋገጠው፣
                  ማንኛውም የመስረተ ልማት ከዕቅድ ነደፋው ጀምሮ አስከ ግንባታው ፍፃሜ
                  ድረስ  የሚጠቀመው  ዘዴ  መሰረተ  ልማቱ  ተግባር  ላይ  ሲውል  የሚኖረውን
                  አካታችነት  ይወስነዋል።  ከዚህም  በተጨማሪ፣  ዓይነታዊ  የመሰረተ  ልማት
                  ግንባታ  መርሆዎችን  መከተል  እንደ  ኢትዮጵያ  ያሉ  ሃገሮች  የሚኖርዋቸውን
                  በኪሳራ የታጠሩ ንብረቶች (stranded assets) ቁጥር ለመቀነስ ያስችላቸዋል።
   111   112   113   114   115   116   117   118   119   120   121