Page 84 - DINQ MAGAZINE OCTOBER 2020 EDITION
P. 84

ከገጽ  78 የዞረ                           የሚያሰባስቡ ተቋማትን መመሥረት                   እንዳይሰብሯት መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
                                             የለብንም ማለት ነው፡፡ እናም መጀመርያ እኔ           ሀገር ከፖለቲካ አመለካከት፣ ከርእዮተ
        ደነገጠ፡፡ «የለም ንጉሥ ሆይ እኔ ብቻዬን           በእነርሱ ቦታ ብሆን ኖሮ ምን አደርግ ነበር?          ዓለም፣ ከፍላጎት፣ ከአስተሳሰብ እና
        ሆኜ እንዲህ ያለውን ሃሳብ አላስበውም፡፡            ብሎ ራስን መጠየቅ ቀጥሎም፣ ልናልፈው               ከምኞት ሁሉ ትበልጣለች፡፡
        ይህንን ጥያቄ ያቀረብነው ከጓደኞቼ ጋር             የሚገባንን ነገር ልንናገርበት እና
        አብረን ሆነን ነውና ከእነርሱ ጋር ተማክሬ           ልንከራከርበት ከሚገባን ነገር ለመየት               የችግር፣ የኋላ ቀርነት፣ የግፍ፣ የጭቆና፣
        መልስ ልስጥ» ብሎ ጠየቀ፡፡                    አለብን፡፡                                የመብት ረገጣ፣ የፍትሕ ማጣት፣
                                                                                   የእኩልነት ማጣት፣ የሰብአዊ መብት
        ንጉሡም «ትናንትና ስናይህ ብቻህን ነበርክ፡፡  አካሄዳችን እና እርማታችን ዋናው ዓላማው                    ማጣት የምንላቸው አይጦች መጥፋት
        ሌላ ጓደኛ አልነበረህም፡፡ ከየት አምጥተህ           ያቋቋምነውን ድርጅት፣ ማኅበር፣ ፓርቲ፣              አለባቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ለዕድገታችን
        ነው የምትማከረው?» ሲሉ ገርሟቸው                ተቋም ማነጽ፣ ማጠናከር፣ እና የተሻለ               ዕንቅፋቶች፣ለኋላ ቀርነታችን ምንጮች
        ጠየቁት፡፡ ያም ገበሬ «ንጉሥ ሆይ                ማድረግ ከሆነ ማናቸውም ነገራችን ምጣዱን             መሆናቸውን የሚክድ የለም፡፡ መጥፋት
        አላዩዋቸውም እንጂ አብረውኝ እነ ብቅል፣            የማይሰብር መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡              የለባቸውም ብሎ የሚከራከርም የለም፡፡
        ጌሾ፣ እነ ደረቆት፣ እነ ጠጅ፣ እነ ጠላ፣ እነ        ያለበለዚያ ግን አንዳንድ ጥቃቅን የስሕተት            ነገር ግን ምጣዱ ሳይሰበር መሆን አለበት፡፡
        አረቄ ነበሩ፡፡ እነርሱ በሌሉበት ይህንን ነገር        አይጦችን እናጠፋለን ብለን የደከምንበትን፣            እነዚህን አይጦች እናጠፋለን ብለን ዛሬ
        ብቻዬን አልናገረውም» ብሎ አሳቃቸው፡፡             ስንት ወዝ እና ልፋት የፈሰሰበትን፣ ስንቶች           ከአንዳንድ ኃይሎች ጋር የምንመሠርተው
        ንጉሡም በአነጋገሩ ተገርመው ምሕረት               እንደ እሳት ነድደው ያሟሹትን፣ የስንቶች             ግንኙነት፣ የምንፈጥረው ኅብረት እና
        አደረጉለት ይባላል፡፡ ለዚህ ነው ለምጣዱ            ድካም እና ሞያ የፈሰሰበትን፣ምጣድ መስበር            የምንዋዋለው ቃል ኪዳን አብሮ ምጣዱን
        ሲባል አይጧን ማሳለፍ የሚጠቅመው፡፡               ይመጣል፡፡                                የሚሰብር እንዳይሆን ደግሞ ደጋግሞ
        ያንን ድፍረት የደፈረው ገበሬው ብቻውን                                                   ማሰብ ያስፈልጋል፡፡
        አይደለም፡፡ እነ አረቄ፣ ጠላ፣እና እነ ጠጅ          ዛሬ በታላላቅ ቤተ እምነቶች የምናየው ጠባይ
        ናቸው፡፡ ስለዚህም አይጧን ከምጣዱ ለይቶ            ለአይጧ ሲባል ምጣዱ ይሠበር የሚል የሞኝ             በታሪካችን ውስጥ ያለፍንባቸው ብዙ
        መምታቱ መልካም ነው፡፡                       አሠራር እየሆነ ነው፡፡ አይጧን ከምጣዱ              አሳዛኝ እና ክፉ ነገሮች አሉን፡፡ እነዚህን
                                             ለይተው መምታት አቅቷቸው ለብዙ ሺ                 ዛሬ ሁላችንም የምንጸየፋቸውን እና
        ሰዎች በማኅበርም ሆነ በድርጅት፣                 ዓመታት የተደከመባቸው ትልልቆቹ ምጣዶች              እንዳይደገሙ የምንታገላቸውን የትናንት
        በኮሚኒቲም ሆነ በፓርቲ ለአንድ ዓላማ፣             እየተሠበሩ ነው፡፡ ያች ገበሬ እናት                ጠባሳዎች ለማረም የምናደርገው ሂደታችን
        በተወሰኑ መሠረታውያን ነገሮች ላይ                ትእግሥትን ገንዘብ አድርጋ፣ ለትልቁ ምጣድ            አይጧን በማጥፋት ሰበብ ምጣዱን
        ትስማምተው አብረው ይሠራሉ፡፡ ሰዎች               ሲባል እስኪ ለጊዜው አይጧን ላሳልፋት               የሚሰብር እንዳይሆን ጥንቃቄ
        አብረው ለመሥራት በሁሉም ነገር ላይ የግድ  ያለችው አይጧ ታስፈልጋለች፣ችግር                           ያስፈልገናል፡፡ ሰው ጠባሳውን አጠፋለሁ
        መስማማት የለባቸውም፡፡ ሌላው ቀርቶ               አትፈጥርም፣እያደረገችው ያለው ነገር ትክክል           ብሎ ቆዳውን አይልጥም፡፡ የሀገሪቱን
        በአንድ ቤት፣ አንድ አካል ሆነው የሚኖሩት           ነው፣ ቤቱን ማውደሟ፣ ያልለፋችበትን ነገር            አንድነት፣ የሕዝቦችን በተዋሕዶ እና
        ባል እና ሚስት እንኳን በመሠረታውያን              መብላቷ፣ ቀበኛ መሆንዋ ተገቢ ነው፤ በዚህ            በተገናዝቦ መኖር፣ የነገን አዲስ ራእይ እና
        ነገሮች ላይ እንጂ በሁሉም ነገሮች ላይ             ሁኔታም መኖር አለባት ብላ አይደለም፡፡              የትውልዱን የወደፊት ጉዞ የምንጋግርባትን
        መስማማት አይችሉም፡፡ ሁለት ከመሆን               ምጧዷን አትርፋ አይጧን ብቻ                     ኢትዮጵያ የምትባለውን የተሟሸች
        የተነሣ የሚመጡ ልዩነቶች አሉና፡፡ ቢያንስ           የምትመታበትን ተስማሚ ጊዜ ለማግኘት                ምጣድ፣ እዚህም እዚያም የሚያስቸግሩንን
        በምግብ ምርጫ ሊለያዩ ይችላሉ፡፡                 እንጂ፡፡ በአንድ ጊዜ ሁለት ጥፋት                 እና አንዳንድ ጊዜም ልናልፋቸው
                                             ላለማጥፋት፡፡                              የሚገቡንን አይጦች በማጥፋት ሰበብ
        እነዚህ ማኅበራት፣ ተቋማት፣ ድርጅቶች እና                                                 መስበሩ ለጫማ ሲባል እግርን
        ፓርቲዎች አንዳንድ ጊዜ ለምጣዱ ሲባል              የሃይማኖት አባቶች የዚህችን እናት ጥበብ እና          እንደመቁረጥ ያለ ነው፡፡
        አይጧን ማሳለፍ አለባቸው፡፡ በትንሽ               ብልሃት ዛሬ ከወዴት ባገኙት?
        በትልቁ በመጨቃጨቅ እና ባለመስማማት፣                                                      እናም እስኪ አንዳንድ ጊዜ «ምእንቲ ዛ
        በሆነው ባልሆነው በመለያየት እና እንደ             የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት አንግበው                 ምጎጎ እታ አንጭዋ ትሕልፍ ለምጣዱ
        አሜባ በመከፋፈል ምጣዱን የሚሰብሩት               የተነሡ ኃይላትም ኢትዮጵያን ያህል ብዙ                    ሲባል አይጧ ትለፍ» እንበል
        ከሆነ በውኑ ይህች ሀገር ተስፋዋ ምንድን            ትውልድ ደክሞ ያሟሻትን ምጣድ፣ ስንቶች
        ነው? ሰዎች ሲሠሩ ይሳሳታሉ፡፡ ከዕውቀት            እንደ እሳት የተማገዱባትን ምጣድ፣ ስንት
        ማነስ ይሳሳታሉ፣ ከመቸኮል ይሳሳታሉ፣              የማንነት፣ የታሪክ፣ የባህል፣ የቅርስ፣ የእምነት
        ትክክለኛ ነገር የሠሩ መስሏቸውም                 እና የወግ እንጀራ ሲጋገርባት የኖረችውን
        ይሳሳታሉ፡፡ ማናቸውንም ዓይነት የሰዎችን            ምጣድ፤ እናጠፋቸዋለን ብለው
        ስሕተት ለመታገሥ የማንችል ከሆነ ሰዎችን            ለሚያስቧቸው አይጦች ሲባል




        84                                                                                  “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ”                                                          ድንቅ   መጽሔት -  ጥቅምት  2013
   79   80   81   82   83   84   85   86   87   88   89