Page 70 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 70

61


         .
        1 1 .  መግቢያ
           መግቢያ
        ካሚሊና  ሳቲቫ  (Camelina  Sativa  L)  የቅባት  እህል  ሲሆን፣  ከጎመን  ዘር  ቤተሰብ


        ውስጥ (Brassicaceae family) የሚመደብ የሰብል ዓይነት ነው፡፡ ሰብሉ በእንግሊዝኛ

        ካሜሊና  የሚል  ስያሜ  የያዘ  ሲሆን  በአማርኛው  ደግሞ  “እ ማዋይሽ”  በሚል  ስም


        ይጠራል፡፡  ይህ  ሰብል  በኢትዮጵያ  ያልነበረ  እና  በቅርቡ  በሀገር  አቀፍ  ደረጀ  በ2011

        እ.ኤ.አ. ወደ ኢትዮጵያ የገባ ሲሆን በ2014 እ.ኤ.አ በግብርና ሚኒስቴር ዘር አጽዳቂ


        ኮሚቴ ተገምግሞና ጸድቆ በዝርያ መመዝገቢያ መጽሃፍ ተመዝግቦ ዝርያው ተለቋል::

        ካሚሊና  መነሻው  ከወደ  አዉሮፓ  እና  መካከለኛው  ኤስያ  እንደሆነ  እና  ለብዙ  ሺህ


        ዓመታት በመልማት የሚገኝ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው፤ ለሰው ልጅ ጤና ተስማሚ

        እና በቅባት እህልነቱ ተወዳጅ የሆነ ሰብል ነው (Davis, 2011)፡፡





        በኢትዮጵያ  እስከ  አሁን  በታዩት  ሙከራዎች  ሰብሉ  በሰፊ  ሥነ  ምህዳሮች  (ከ1600-


        3200 ሜትር ከባሕር ጠለል በላይ) እና የአየር ንብረት (ከሞቃታማ እስከ ውርጫማ)

        ውስጥ ተላማጅ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡  በደጋማው አየር ንብረት ደቡብ ጎንደር እና


        ሰሜን ወሎ (በሊቦ ከምከም፣ በፋርጣ፣ እስቴ፣ በላይ ጋይንት፣ ዋድላ እና ሰሜን ሸዋ)፤

        በቆላማው የስምጥ ሸለቆ (አለምጤና) እንዲሁም በደቡባዊው የሀገሪቱ ከፊል መጠነኛ


        ኮምጣጣነት  ባለው  የአፈር  አካባቢ  (ሀዲያ)  ተፈትሾ  መልካም  ውጤት  የሰጠ  ሰብል

        ነው፡፡ ሰብሉ የመሬት ለምነትን በማሻሻል፤ተባይና በሽታዎችን የመቋቋም አቅሙ





 የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል  የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   65   66   67   68   69   70   71   72   73   74   75