Page 73 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 73
64
• የካሚሊና ሰብል በሀገራችን ያልተስፋፋ በመሆኑ የተሻሻሉ አሰራሮችና
ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ አርሶ አደሩን
ተጠቃሚ ስለሚያደርግ፡፡
• የተሻሻሉ አሰራርና ቴክኖሎጂዎችን ምክረ ሀሳብ በአርሶ/ከፊል እንዲሰርፅ ተከታታይ
የሆነ ምክርና ክትትል ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፡
• በዘርፉ ከሚንቀሳቀሱ የምርምርና የተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመስራት በምግብ
ሰብል ልማት የሚስተዋሉ የክህሎት ክፍተቶችን መሙላት ማስፈለጉ፤
• የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ዋስትና በማረጋገጥ ጤናማ አምራች ማህበረሰብ
ለመፍጠር ማስፈለጉ፤
ሉ ገ
ብ
ሰ
ድ አ
መ
ም
ቅ
ታ
ጽ
መላ
ና የ
2 . የሰብሉ ገጽታና የመላመድ አቅም
2
የ
.
ካሚሊና ሳቲቫ (Camelina sativa (L) Crantz) እንደጎመን ዘር (Canola & mus-
tard) ሁሉ የጎመን ቤተሰብ ነው፡፡ ይህ ሰብል እንደ ተልባ የፍሬው አቃፊ ተመሳሳይነት
ያለው ነው። ካሚሊና በሜዲቲራኒያን እና ማዕከላዊ ኤሲያ አካባቢዎች የቀደምትነት
መገኛ ሥፍራው ሲሆን የዓመታዊ ሰብል ምድብ ውስጥ ይገኛል (Fleenor, richard
a. 2011) ፡፡
የፍሬ አቃፊያቸው /ምስል 1/ ከ6-14 ሚ.ሜትር ርዝመት ያለውና ከ8-10 ቢጫ ወይም
ቡናማ ቢጫ ፍሬዎችን የያዘ እና አራት ማዕዘን ቅርፅና ሻካራ ገጽታን ያያዘ ነው፣
(ምስል1/MoA, Crop Variety Registration, 2014)፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል