Page 15 - Ayinie Magazine
P. 15

እንመክራቸዋለን፡፡  በሌላ  መልኩ  ዓይነ
                                                                                ስውርነትን በመከላከል ላይ በተቻለ መጠን
                                                                                ህብረተሰቡን  የማስተማር  ጥረት  እያደረግን
                                                                                ነው፡፡ ሁለቱንም ወገኖች ነው የምናስተምረው
                                                                                (ታማሚውንና       ቤተሰቡን)፡፡     ለምሳሌ
                                                                                ትራኮማ  የሚተላለፍ  በሽታ  ነው፡፡  ስለዚህ
                                                                                ቤተሰብ  ራሱን  ከትራኮማው  መከላከል
                                                                                አለበት፡፡  ሌላ  ምሳሌ  መነፅር  የሚያደርግ
                                                                                ዓይነ  ስውር  ለሙከራ  እያለ  ለልጆች
                                                                                መስጠት፣ አልባሌ ቦታ ማስቀመጥና ልጀች
                                                                                እንዲሞክሩት ማድረግ የለበትም፡፡ መጠንቀቅ
                                                                                አለበት፡፡  እነዚህን  ትምህርቶች  ለዓይነ
                                                                                ስውራኑ  እንሰጣለን፡፡  ሌላውን  ማህበረሰብ
                                                                                ደግሞ  ስለ  ዓይነ  ስውርነት  በአጠቃላይ
                                                                                ትምህርት  እየሰጠን  ነው፡፡  ከተለያዩ
                                                                                ድርጅቶች  ጋር  ለምሳሌ  ከኦርቢስ  ጋር
                                                                                በመተባበር በራሪ ወረቀቶችን በመማዘጋጀት
                                                                                ፣  አውደ  ጥናቶችን  በማድረግ  በየክልሉ
                                                                                ስንሰራ ነው የቆየነው፡፡ ዛሬም እንሰራበታለን፡
                                                                                ፡ ምክንያቱም ከዓላማችን አንዱ ማስተማር
                                                                                ስለሆነ፡፡

                                                                                በነገራችን  ላይ  ምን  ያህል  ዓይነ  ስውራን
                                                                                በአገራችን አሉ?
                                                                                ጤና  ጥበቃ  ሚኒስቴር  በ2006  እኤአ
                                                                                መስከረም  ወር  ላይ  ያወጣው  ጥናት  አለ፡፡
                                                                                ከትራኮማ ጋር ተያይዞ ነው ጥናቱ የተደረገው፡
                                                                                ፡ 1.2 ሚሊዮን ሙሉ፣ 2.2 ከፊል ዓይነ
                                                                                ስውራን  በድምሩ  3976500  እንደሆነ
                                                                                ነው  የተገለፀው፡፡  እስካሁን  የምንጠቀመው
                                                                                ይህንኑ አሃዝ ነው፡፡
                                                                                አንተ እንደጠቀስከው በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር
                                                                                መረጃ መሰረት በዚህ ጥናት ከ3 መቶ ሺህ
                                                                                የሚበልጡት ዓይነ ስውራን መዳን በሚችለው
                                                                                በብሌን ጠባሳ ምክንያት ዓይነ ስውር የሆኑ
                                                                                ናቸው፡፡  ዓይን  ባንኩ  ከተቋቋመበት  ጊዜ
                                                                                አንስቶ ከ1600 በላይ ለሆኑ ዓይነ ስውራን
                                                                                ብቻ ነው (እስካሁን ባለው መረጃ) ንቅለ
                                                                                ተከላ ተደርጎ ብርሃን እንዲያዩ ያስቻለው፡፡
                                                                                በዚህ ላይ ምን አስተያየት አለህ?

                                                                                                       13
   10   11   12   13   14   15   16   17   18   19   20