Page 16 - Ayinie Magazine
P. 16

በዚህ ብቻ ሳይሆን በሌላው ነገርም እንኳን ቢሆን ፍላጎትና አቅርቦት
                                                            የሚመጣጠኑ  ሊሆኑ  አይችሉም፡፡  ከተመጣጠነም  በጣም  አደገኛ
                                                            ነው  የሚመስለኝ፡፡  ምክንያቱም  ዕድገት  ይቆማል፡፡  ዕድገት  የሚኖረው
                                                            ፍላጎት ሁሌም ወደፊት ሲፈጥን ነው፡፡ ምክንያቱም አቅርቦት ፍላጎትን
                                                            እየተከተለ  ሲሄድ  እድገት  ይመጣል፡፡  እንደተባለው  ደግሞ  ጥረቱ
                                                            በመጀመሩና ፈርቶ ባለመተው የዚህን ያህል ውጤት ተገኝቷል፡፡ አሁንም
                                                            ግን የሚለግሱ ወገኖች ቢበዙ የንቅለ ተከላ ባለሙያዎች ካልበዙ አሁንም
                                                            ኪሳራ ነው፡፡ ስለዚህ ባለሙያዎች መብዛት ይኖርባቸዋል፡፡ እዚያ ላይ
                                                            ነው ትኩረት ተደርጎ መሰራት ያለበት፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራውም
                                                            አሁንም ቢሆን መቀጠል ይኖርበታል፡፡ ይሄ ሁሉ ሆኖ ደግሞ የገንዘብ
                                                            ችግር መፈጠሩ አይቀርም፡፡ ዛሬ ገንዘብ ለማሰባሰብ ብዙ ስራ እየተሰራ
                                                            መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ግን በቂ አይሆንም፡፡ የዚህ ዓይነት ጥረት የትም
                                                            አያደርስም፡፡  ስለዚህ  አቅጣጫ  መለወጥ  አለበት፡፡  መንግስት  ትኩረት
                                                            ሰጥቶት የተወሰነ የሚያደርገው ድጋፍ አለ፡፡ ግን የበለጠ ወደፊት በበጀት
                                                            ድጋፍ ተደርጎለት እንዲቀጥል መንግስት ቢይዘው ጥሩ ነው የሚሆነው፡፡
                                                            ምናልባት ቦርዱ በዚህ በኩል የበለጠ ትኩረት ቢያደርግ የተሳካ ውጤትና
                                                            ዘላቂ መፍትሄ የሚሆን ይመስለኛል፡፡

                                                            በአንተ እምነት ለዓይን ባንኩም ሆነ ለእናንተ ለባለአደራ ቦርዱ አባላት
                                                            ከባዱ ተግዳሮት ምንድን ነው?

                                                            ከባዱ ነገር የሰው ሀይልና ገንዘብ ነው፡፡ በእርግጥ የቦርዱ አባላት የተወሰኑ
                                                            ጊዜያት ነው እየተሰባሰብን አንዳንድ ውሳኔዎችን የምንወስነው፡፡ ከፍተኛ
                                                            ስራዎችን የሚሰሩት ሰራተኞችና የማኔጅመንት አባላት ናቸው፡፡ ግን ዛሬ
                                                            እነሱ ባሉበት ሁኔታ ሊኖሩ አይችሉም፡፡ ስለዚህ በእነሱ ላይ መጨመር
                                                            ያስፈልጋል፡፡ እነሱንም የሚተካ ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ የሰው ሀይል ስል
                                                            ሙያተኛ የሆነ ሰው ለማለት ነው፡፡

                                                            በመጨረሻ መልዕክትህን እናጠቃለው ቆይታችንን፡፡

                                                            አሁንም ቢሆን የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ምንጊዜም ሊቀጥል ይገባል፡
                                                            ፡  የባህል  ጉዳይ  አለ፡፡  እሱን  መቋቋም  እንዲቻል  ግንዛቤ  ማስፋፋት
                                                            ያስፈልጋል፡፡  ሌላው  የህግም  ጉዳይ  ስላለ  ከመንግስት  ጋር  መነጋገር
                                                            ያስፈልጋል፡፡ አንዳንድ ማስተካከያዎች ማድረግ ያስፈልጋል፤ እንቅፋት
                                                            እንዳይሆኑ፡፡ ስለዚህ እነዚህ የሚሰሩ ከሆነ ወደፊት ዓይን ባንኩ የተሻለ
                                                            እየሰራ የሚሄድ ይመስለኛል፡፡

                                                            ለቆይታችን በጣም አመሰግናለሁ!

                                                            እኔም አመሰግናለሁ!




            14
   11   12   13   14   15   16   17   18   19   20   21