Page 113 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 113

104

               ሻሉ አመ
                      ራረት ዘዴዎች
            የተሸ

          .
        4
        4 .  የተሸሻሉ አመራረት ዘዴዎች
        4.1. ማሳ መ
        4.1. ማሳ መረጣ
                ረጣ
        ለዘር (ለፍሬ) ተኮር ሰብል የሚሆን ማሳ በምንመርጥበት ጊዜ ታሳቢ የምናደርጋቸው
        ጉዳዮች፡-  የአፈሩ  ዓይነት  ከገንቦሬ  እስከ  መረሬ/ዋልካ  ሊሆን  ይችላል፣  የመሬቱ

        ተዳፋትነት መጠነኛ ቢሆን ውሃ ለማጠንፈፍ ያግዛል፡፡ የማሳው ቀደም ታሪክ


        መመርመርና በቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ (ሲናር እና ሌሎች መሰል የብርዕ ሰብሎች)

        ያልተመረቱበት  ቢሆን  ይመረጣል፡፡ ይኸውም  ከተመሳሳይ  ዝርያዎች  የሚተላለፉ


        በሽታዎችንና እንደ እንክርዳድ የመሳሰሉ አረሞችን ወረራ ለመከላከል ነው፡፡ ከሰብል

        ፈረቃ አንጻር እንደየአካባቢዉ ተስማሚነት የጥራጥሬ ሰብሎች (ቦለቄ፣ አተር፣ ባቄላ፣


        የእርግብ አተር፣ የላም አተር) ወይንም ጎመንዘር የመሳሰሉት ቢቀድሙ ይመረጣል::

        በማሳ  መረጣ  ወቅት  የሚደረገው  ጥንቃቄ  ምርታማነትን  ከመጨምር  በተጨማሪ


        ጥራት  ያለው  ሰብልን  ለማምረት  ያስችላል።  በተለይም  ከማሳው  የሚገኘውን  ምርት

        ለሚቀጥለው የሰብል ዘመን ለምርትነት የምንጠቀም ከሆነ በምንም ሁኔታ የምግብ


        ሲናር በቀዳሚው አመት የተዘራበት ማሳ መዘራት የለበትም።


        4.2. የማሣ ዝግጅት
        4.2. የማሣ ዝግጅት


        ለምግብ ሲናር አዝመራ የሚውል ማሳ ዝግጅት በመሰረቱ በአፈሩ ዓይነት ይወሰናል፡፡


        ሲናር በፍሬ ግዝፈቱ እና በአስተዳደጉ እንደ ስንዴ እና ገብስ ተመሳሳይ ስለሆነ የማሳ

        ዝግጅቱም ተመሳሳይ ነው፡፡ መረሬ አፈር የዝናብ ወቅት ሲጀምር ዉሃ በብዛት ከማቆሩ


                                        የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል     የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   108   109   110   111   112   113   114   115   116   117   118