Page 115 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 115
106
4.3. ዘር መረጣ
4.3. ዘር መ ረጣ
የዘር ጥራቱና የዘር ብቅለቱ የተመሰከረለት የምግብ ሲናር ዓይነት ከታማኝ ምንጭ
ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ በሀገራችን ለምግብ የሚሆን የሲናር ዓይነት በምርምር የመምረጥ
ሂደት በጅማሮ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ለጊዜዉ በቅርቡ የተለቀቁ ዝርያዎችን መጠቀም
ይቻላል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የተሻሻሉ ዝርያዎችን መጠቀም የሲናር ምርትን እስከ
50% ይጨምራል።
በአሁኑ ወቅት የሲናር አምራች ገበሬዎች የሚጠቀሙት ዝርያ ለመኖነት የተለቀቀ
በመሆኑ የዘር ምርታማነቱ አነስተኛ ነው። ነገር ግን ለምግብ ሲናርነት በምርምር
ማዕከላት የተለቀቁ ዝርያዎች ምርታቸው ከፍተኛ ከመሆናቸው በተጨማሪ የምግብ
ንጥረ ነገር ይዘታቸውም ከፍተኛ ነው። ከዘር ምርታቸው በተጨማሪም የገለባ
ምርታማነታቸው ጥሩሩ በመሆኑ አርሶ አደር ቢጠቀማቸው ከፍተኛ ጠቀሜታ ያገኛል።
በምርምር ስርአቱ የተለቀቁ እና የተመዘገቡ የምግብ ሲናር ዝርያዎችን በሰንጠረዥ 1
መመልከት ይቻላል።
እና
ነዋ፣ የካሚሊና
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
የኬ