Page 120 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 120
110
የዘር ጥልቀት
ለዘር በቂ የአፈር እርጥበት ካለ ዘሩ 3-4 ሳ.ሜ ጥልቀት ላይ ይዘራል፡፡ ከዚህ በላይ
ዘሩ በአፈር ከተቀበረ የመብቀል አቅሙን ስለሚቀንሰው የሰብሉን አጠቃላይ አቋም
ያልተስተካከለ ሲያደርገው ከተጠቀሰው በታች በበቂ ሁኔታ አፈር ካልለበሰ ደግሞ
የመወለድ አቅሙን ከመቀነሱም በላይ በደካማ የሆነ የስር እድገት ምክንያት በቀላሉ
ሊወድቅ ይችላል፡፡
4.7 የአዘራር ዘዴ
4.7 የአዘራር ዘዴ
እስከአሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የምግብ ሲናር የሚዘራው በብተና ሲሆን በተቻለ
መጠን በብተና ሲዘራ ለሚዘራው ማሳ ተመጥኖ የመጣው ዘር በአግባቡ በተመጣጣኝ
መልኩ እኩል መዳረስ ይኖርበታል። በእኩል ተበትኖ የተዘራ ሰብል አላስፈላጊ የእጽዋት
ሽሚያን በማስቀረት ጥሩ ምርት እንዲገኝ ይረዳል። ስለሆነም በምርምር የሚመከረውን
የዘር መጠን እና አዘራር መከተል ይገባል።
የምግብ ሲናር በመስመር በዘር መዝሪያ ማሽን ሲዘራ በእጽዋት መካከል 0.10 ሳ.ሜ
እና በመስመር መካከል 20 ሳ.ሜ መሆን ይኖርበታል። ነገርግን በሀገራችን ገበሬ
ሁኔታ የተገለጸውን በመስመር መካከል የሚያስፈልገውን የርቀት መጠን መጠበቅ
ስለሚያስቸግር ገበሬው በመስመር በሚዘራበት ወቅት በሚከተለው መልኩ መሆን
ይኖርበታል። በመስመር በምንዘራበት ወቅት በሬው ለእርሻ ያወጣውን ፈሰስ
በመከተል ማዳበሪያው በተጨመረበተ ቦታ ላይ ዘሩን መጥኖ በማንጠባጠብ የዘር ሥራ
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል