Page 125 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 125
115
ምርት መቀነስ አንዱ አይነተኛ ምክንያት በአንድ ማሳ ላይ ተመሳሳይ ሰብልን እና
በአንድ ምድብ የሚገኙ ሰብሎችን (የብርዕ ሰብሎችን) በማከታተል መዝራት ነው።
ሰብልን ማፈራረቅ የአፈር ለምነት ከመጠበቅ በተጨማሪ የቀጣዩን ሰብል (የሲናር)
ምርታማነትን ያሻሽላል፡፡ በተጨማሪም ሰብልን ማፈራረቅ የአረም ጥቃት፣ ነፍሳት
ተባዮችና አፈር ወለድ በሽታዎች በመቀነስ የሰብል ምርታማነትን ይጨምራል።
የምግብ ሲናር ናይትሮጅንን ከአየር የሚሰበስቡ ሰብሎችን (ጥራጥሬ ሰብሎችን)
አስከትሎ በመዝራት የሚጨመረው ዩሪያ መጠን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ ስለሆነም
ከሲናር በፊትም ሆነ በኋላ የብርዕ ሰበሎችን ከመዝራት ጥራጥሬዎችን ( ባቄላ፣
አተርና ሽምብራ)፤ ተልባ፣ ኑግ፤ጎመንና ድንች የመሳሰሉትን ሰብሎች መዝራት ከፍተኛ
ጠቀሜታ ያስገኛል:፡ ሲናርን ከነዚህ ሰብሎች ጋር በየሁለት ዓመቱ በማፈራረቅ ዘላቂ
ምርታማነትን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
6. የሰብል ጥበቃ ዘዴዎች
6. የሰ ብ ል ጥበቃ ዘዴዎች
6.1.
6.1. የአረም ቁጥጥር
የአረም ቁጥጥር
በተለያዩ ሲናር አምራች አካባቢዎች በከፍተኛ ጎጅነታቸው የተመደቡት አረሞች
ግሸ፣ ሽዩ፤ ሙጃና መጭ ሲሆኑ መካከለኛ ጉዳት በማድረስ ቦረን፤ አሽክት፤ የውሻ
ሰንደዶ፤ አቀንጭራና ሌሎች ቅጠለ ሰፋፊና የሳር አረሞች ናቸው፡፡ በሚገባ ታርሶ
የለሰለሰና ከአረም የጸዳ ማሳ ማዘጋጀት፤ ከአረም ነጻ የሆነ ዘር መጠቀም፤ በመስመርና
ቀድሞ መዝራት፤ ከተዘራ ከ18-20 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ በእጅ በመንቀል ማረም
አስፈላጊ ነው። እንዲሁም ሁለተኛ አረም ከ30-40 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ሊከናወን
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል