Page 127 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 127

117
        አስፈላጊ የሆኑ የጥንቃቄ አልባሳትን መጠቀም ይኖርበታል።


        ማሳሰቢያ፡- ስለኬሚካሉ አጠቃቀም በኬሚካሎች መያዣ ላይ ያለውን መግለጫ

        በተጨማሪ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡


        6.2. የተባይ ቁጥጥር
        6.2. የተባይ ቁጥጥር


        በኢትዮጵያ በአዝመራ ወቅት በምግብ ሲናር ላይ የሚታይ ተባይ አይነት የሌለ ሲሆን

        ይህም  የሆነው  ሲናር  የሚመረትበት  አካባቢ  የመስክ  ተባይ  የማይታይበት  ደጋማው


        አካባቢ በመሆኑ ነው። በእስካአሁን በተካሄደው ምልከታ በምግብ ሲናር ላይ ያጋጠሙ

        የተባይ አይነቶች አልተመዘገቡም። አልፎ አልፎ የዝናብ እጥረት በሚከሰትበት ወቅት


        ክሽክሽ የሚባል ተባይ ሊከሰት ይችላል። ይህን ተባይ ለመከላከል ሴሌክሮን 0.5-0.6

        ሊትር ለ1 ሄክታር ወይም ዳይሜትዮይት 2ሊትር ለሄክታር በ200 ሊትር ውሀ በጥብጦ


        መርጨት ተገቢ ነው።

        ማሳሰቢያ፡- ስለኬሚካሉ አጠቃቀም በኬሚካሎች መያዣ ላይ ያለውን መግለጫ


        በተጨማሪ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡

        ሲናር  ከተሰበሰበ  በኋላ  ከሚያጠቁት  ተባዮች  ውስጥ  ዋና  ዋናዎቹ  ነቀዝ፣  ጥንዚዛ፣


        የእሳት እራት እና አይጥ ሲሆኑ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ከዚህ ቀጥሎ በሰንጠረዡ

        ላይ የተጠቀሱትን ዘዴዎች መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን ተባዮች ለመቆጣጠር


        በሰንጠረዡ ከተቀሱት ዘዴዎች በተጨማሪ ዘመናዊ የእህል ማከማቻ ዘዴ መጠቀም

        ይቻላል፡፡





 የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል  የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   122   123   124   125   126   127   128   129   130   131   132