Page 126 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 126
116
ይችላል:: የፀረ አረም ኬሚካሎችን ስንጠቀም በምክረ-ሃሳቡ ላይ በተገለጸው መሠረት
መሆን ይኖርበታል፡፡ የምግብ ሲናር ከሳር ዝርያዎች አንዱ ስለሆነ የሳር አረም ማጥፊያ
ኬሚካሎችን መጠቀም በጭራሽ አይመከረም። ስለሆነም በምግብ ሲናር ላይ የሳር
አረምን ለማጥፋት ብቸኛው መንገድ በእጅ ማረም ብቻ ነው። በምክረ ሃሳቡ ከተገለጸው
ውጭ መጠቀም አረሞች ኬሚካሉን እንዲላመዱ ስለሚያደርጋቸው ለወደፊት የአረም
ቁጥጥርን አስቸጋሪ ያደርጋል፡፡ አረምን ለመቆጣጠርና ከአረም የፀዳ ሰብል ለማምረት
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተግባራት ማከናዎን ያስፈልጋል፡፡
• በሚገባ ታርሶ የለሰለሰና ከአረም የጸዳ ማሳ ማዘጋጀት፣
• ከአረም ነጻ የሆነ እና የጥራት ደረጃው የተመሰከረለት ዘር መጠቀም፣
• በእጅ የሚታረም ከሆነ እንደ አስፈላጊነቱ ከ1-2 ጊዜ ማረም፡፡
• 1ኛ አረም ሰብሉ ከተዘራ 18 - 20 ቀናት ፣
• 2ኛ አረም ከ30 - 40 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ይከናወናል፡፡
በኬሚካል መከላከል
በኬሚ ካል መከላ ከል
ሲናር ከሳር አረም ዘሮች የሚመደብ ስለሆነ በምግብ ሲናር ውስጥ የሳር አረምን
ለመቆጣጠር ብቸኛው መፍትሄ በእጅ ማረም ብቻ ነው። ቅጠለ ስፋፊ አረሞችን
ለመቆጣጠር 2.4 ዲ መጠቀም የሚቻል ሲሆን አጠቃቀሙም 1ሊትር በ200 ሊትር
ውሀ በመበጥበጥ ለ 1 ሄክታር መርጨት ነው። የአረም መድሃኒቱን በምንረጭበት ጊዜ
አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። በመሆኑም ኬሚካሉን የሚረጨው ሰው
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል