Page 122 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 122

112
                               ጠን
                 በሪያ ዓይነትና መ
        4.8. የማዳበሪያ ዓይነትና መጠን
        4.8. የማ
               ዳ
        ዩሪያ
        ዩሪያ
        የምግብ  ሲናር  የናይትሮጅን  ፍላጎት  ከዘር  ፍሬ  ሙሉነት  እና  ከፍሬ  ክብደት  ጋር

        የተሳሰረ  እንደሆነ  ጥናቶች  ያመላክታሉ፡፡  ከፍተኛ  መጠን  (ከ100  ኪ/ግ/ሄክታር


        በላይ የሆነ ናይትሮጅን) መጠቀም ፍሬ ተሸካሚ ዛላን በማበራከት ለዘር ፍሬ ይዘት

        አስተዋጽኦ  ያደርጋል፡፡  ነገር  ግን  በተቃራኒው  የናይትሮጅን  መብዛት  የዘር  ፍሬን


        ክብደትና የዘር ሙሌትን በመቀነስ በዘር ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያመጣል፡፡ የዘር

        መዝሪያ ወቅትም ለናይትሮጂን አጠቃቀም፤ አደራረግ፤ ለዘር መሙላትና ጥራት ላይ


        ተጽዕኖ አለው፡፡ የተሟላ የዘር ፍሬ ጥራት (ሙሉዕነት) ባልዘገየ የዘር ወቅት ከተዘራ

        እና የናይትሮጅን ልገሳው መጠነኛ ከሆነ ሰብል እንደሚመረት ጥናቶች ያመላክታሉ::


        ስለዚህም  ዘግይቶ  የተዘራ  የሲናር  ሰብል  የዘር  ፍሬ  ጥራቱን  ለመጠበቅ  የናይትሮጅን

        ልገሳው ከመደበኛው እስከ ግማሽ ድረስ መቀነስ እንዳለበት ይመከራል፡፡ በአጠቃላይ


        ለምግብ  ሲናር  የናይትሮጅን  ማዳበሪያ  ልገሳ  መጠን  ከ  63  ኪ.ግ./ሄክታር  የምርት

        ይዘትና ጥራት አመርቂ እንደሚሆን ይታወቃል፡፡ ይህ ማለት በሄክታር 112 ኪ.ግ ዩሪያ


        ማዳበሪያ ይሆናል።  የናትሮጅን ማዳበሪያ ዩሪያ ( Urea ) አጠቃቀም 1/3ተኛው በዘር

        ወቅት ሲሆን ቀሪው 2/3ተኛ ሰብሉ በሚወልድበት ጊዜ ወይም ከዘር በኋላ ከ35-45


        ቀን ባለው ጊዜ መሆን ይኖርበታል።









                                        የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል     የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   117   118   119   120   121   122   123   124   125   126   127