Page 121 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 121
111
ማከናወን ይገባል። በሁለት መስመሮች መካከል 30 ሳ.ሜ እንዲሆን ጠባብ ድግር (30
ሳ/ሜ ስፋት ያለው ድግር) በመጠቀም ገምተን መዝራት ያስፈልጋል፡፡ በሬው በእርሻ
ባወጣው መስመር ሲሄድ የተዘራውን ሲመለስ እንዲያለብስው ይደረጋል፡፡
የምግብ ሲናርን በመስመር ለመዝራት የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ይቻላል።
• የተለያዩ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እንዲቻል ለምሳሌ አረም፣ ማዳበሪያ
በአግባቡ ያለችግር በጎን ለመጨመር እና ማንኛውንም የግብርና ሥራዎችን
ለመተግበር እንዲቻል በመስመር መካከል ያለው ስፋት 30 ሳ.ሜ. መሆን አለበት፣
• ታርሶ ለዘር በተዘጋጀው ማሳ ላይ ከ7 - 10 ሳ/ሜ ጥልቀት ያለው ቦይ ማውጣት
• በወጣው ቦይ ውስጥ ለምግብ ሲናር ከተመከረው የማዳበሪያ መጠን (ኤን.ፒ.ስ
(NPS) እና ዩሪያ በመቀላቀል በተመሳሳይ መልኩ በወጣው መስመር ላይ መጨመር
እና አፈር ማልበስ ያስፈልጋል፡
• በተመለሰው አፈር ላይ እንደሚዘራው ለእያንዳንዱ መስመር የሚያስፈልግ ዘር
መጥኖ ማዘጋጀት፣
• ለመስመር ተመጥኖ የተዘጋጀውን ዘር በማንጠባጠብ (drilling) መዝራት፣
• ለዘር በቂ የአፈር እርጥበት ካለ ዘሩ ከ3-4 ሳ.ሜ ጥልቀት ላይ ይዘራል፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል