Page 123 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 123
113
ኤን.ፒ፣ኤስ
ኤን.ፒ፣ኤስ
የኤን.ፒ፣ኤስ. ማዳበሪያ ለምግብ ሲናር ለዘር መጠንና ጥራት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው::
ስለሆነም ከ 23 ኪ.ግ. ፎስፌት/ሄክታር በዘር ጊዜ መጠቀም ይመከራል፡፡ የፎስፌት
ማዳበሪያ ምንጭ ኤን.ፒ.ስ (NPS) ሲሆን አጠቃቀሙም 60 ኪ.ግ ኤን.ፒ.ስ በሄክታር
በዘር ወቅት መጠቀም ይቻላል።
የተፈጥሮ ማዳበሪያ እና ኖራ አጠቃቀም
የተፈጥሮ ማ ዳበሪያ እና ኖራ አጠቃቀም
በኢትዮጵያ ለግብርና ስራ ከሚውለው መሬት ውስጥ 43% አሲዳማ አፈር ነው፡፡
አፈሩ አሲዳማ ነው የሚባለው የሀይድሮጅን፣ አሉሙኒየምና ብረት የተባሉት ንጥረ-
-ነገሮች ክምችት ሲበዛና በሌላ በኩል ደግሞ የካልሲየም፣ ፖታሲየም፣ ማግኒዚየም
እና የመሳሰሉት ንጥረ-ነገሮች መጠን ሲያንስ ነው፡፡ እስካሁን ባለው ውስን መረጃ
መሰረት አሲዳማ አፈሮች በሁሉም የአገራችን አፈር ዓይነቶች የሚገኙ ቢሆንም በብዛት
በአሲዳማነት የሚታወቁት የአፈር አይነቶች /እንደ ስፋታቸው መጠን ከከፍተኛው
ወደ ዝቅተኛው/ Nitosols,Vertisols, Cambisols, Luvisols, Lithosls, Acris-
tols/ በመባል የሚታወቁት ናቸው፡፡ እነዚህ የአፈር አይነቶች ለም የሆኑና ምርት
በመስጠት የሚታወቁ ዋና የእርሻ መሬቶች ናቸው፡፡ በእርግጥ የተጠቀሱት የአፈር
አይነቶች የሚገኙባቸው አካባቢዎች ሁሉ አሲዳማ ባይሆኑም የመጀመሪያው Nitosol
/ቀይ አፈር/ በመባል የሚታወቀው ግን በአገራችን ካለው የቀይ አፈር መጠን ከ80
በመቶ ያላነሰው አሲዳማ ነው፡፡ አንድ የእርሻ መሬት አሲዳማ መሆኑንና አለመሆኑን
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል