Page 118 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 118

108
                 ከም
        4.4. ዘርን ማከም
        4.4. ዘርን ማ


        ሲናር  ለፍሬ  ሲመረት  የእድገት  ጊዜው  ከብቅለት  አስከ  ፍሬ  ብስለት  ረዥም  ስለሆነ

        በዚህ ወቅት በተለያዩ የሻጋት እና የዋግ በሽታዎች ሊጠቃ ይችላል፡፡ ስለዚህ ከበሽታ


        የጸዳ ዘር ከመጠቀም በተጨማሪ ዘሩን በፀረ-ሻጋት ኬሚካል ማከም የበሽታውን ክስተት

        ይቀንሳል፡፡  በተለይም  በዘር  የሚተላለፉ  በሽታዎችን  እንደ  አረማሞ  ያሉ  በሽታዎችን


        ለመቆጣጠር ዋነኛ መንገድ ነው። የአረማሞ በሽታን ለመከላከል ፕሮሲድ ፕላስ እና

        ዳይናሚክን መጠቀም ይቻላል። አጠቃቀሙ 2.5 ኩንታል ዘርን በ200 ግ.ም ኬሚካል


        በማሸት መጠቀም በዘር የሚተላለፉ በሽታዎችን መከላከል ያስቻላል።



        4.5. የዘር ወቅት
        4.5. የዘር ወቅት


        እንደማንኛውም በዝናብ የሚለማ ሰብል ሁሉ የምግብ ሲናርም የሚዘራው የክረምቱ

        ዝናብ  በአስተማማኝ  ሁኔታ  መግባቱ  ሲረጋገጥ  ነው፡፡  ቢሆንም  አርሶ  አደሩ  ካለው


        ልምድ የረጅም ጊዜ የዝናብ፤ የአየር ሙቀት እና የውርጭ መለዋወጥ አንጻር አመች የዘር

        ወቅቶችን ለመወሰን የአርሶ አደሩንም ልምድ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በወቅቱ የተዘራ


        ሲናር የምርት ይዘት (grain yield፣ የፍሬ ክብደት (grain density) እና ምሉዕነት

        (plumpness) ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ሆኖም የተለያዩ ዓላማዎችን ለማሳካት ከተለመደው


        የዘር ወቅት ሊቀድም ወይንም ሊዘገይ ይችላል። ተሻሽለው የመጡ ዝርያዎችን ስንጠቀም

        ዝርያዎችን የሚደርሱበትን ቀን ባገናዘበ ሁኔታ መዘራት ይኖርባቸዋል።





                                        የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል     የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   113   114   115   116   117   118   119   120   121   122   123