Page 129 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 129

119
         ማሳሰቢያ፡- ስለኬሚካሉ አጠቃቀም በኬሚካሎች መያዣ ላይ ያለውን መግለጫ በተጨማሪ


                                   ማንበብ ያስፈልጋል፡፡

        ከላይ ከተጠቀሱት ኬሚካሎች በተጨማሪ ሌሎች ጸረ ተባይ መድሃኒቶችን በግብርና


        ሚ/ር ምዝገባ ውስጥ የተዘረዘሩትን መመልከት ተገቢ ነው፡፡


        6.3. የበሽታ ቁጥጥር
        6.3. የበሽታ ቁጥጥር

        የሲናር ዋና ዋና በሽታዎች በአውዳሚነት ቅደም ተከተል፡- የቅጠል ሻጋታ (Leaf rust/

        Crown rust)፣ የአገዳ ሻጋታ (Stem rust)፣ የገብስ ቢጫ አቀጭጭ ቫይረስ (BYDV)፣


        አረማሞ እና የቅጠል ዋግ (Fungal leaf spot) ናቸው፡፡ እነዚህን በሽታዎች ለመከላከል

        ዓይነተኛው ዘዴ በተፈጥሮ የመቋቋም ባህርይ ያላቸዉና ከምርምር ተቋሞች የሚለቀቁ


        አዳዲስ ዝርያዎችን ተከታትሎ በመውሰድ መጠቀም ነው፡፡ ሌላው የመከላከያ ዘዴ

        ለበሽታ መዛመት ሰበብ የሚሆኑ  ምክንያቶችን ማስወገድ ነው፤ ለምሳሌ በማሳው


        ላይ ውሃ መተኛት፣ የሰብል ፈረቃ አለመጠቀም፣ በትክክለኛው ወቅት አለመዝራት፣

        የተበከለ ዘር መዝራት የመሳሰሉት ሲሆኑ ለእነዚህ አጋላጭ ክስተቶች እልባት መስጠት


        የበሽታዎችን  ጫና  ወይንም  ድግግሞሽ  ይቀንሳል፡፡  የመጨረሻውና  ውድ  የሆነው

        መፍትሔ ደግሞ ጸረ-ሻጋት ኬሚካሎችን መጠቀም (ዘሩን ማከም፣ ሰብሉን መርጨት)


        ሲሆን ይህም ከአዋጭነት አንጻር መታየት ይኖርበታል፡፡ የሚከተሉትን የኬሚካል

        መድሀኒቶች መጠቀም ይቻላል።









 የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል  የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   124   125   126   127   128   129   130   131   132   133   134