Page 111 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 111

102
                ን የሚመ
             ብሉ
          .

            ሰ
                                   ዳሮ
                              ነ-ምህ
                       ረትበት ስ
                                     ች

        3
        3 .  ሰብሉን የሚመረትበት ስነ-ምህዳሮች
        3.1. ከባህር ጠለል በላይ ከፍታ
        3.1. ከባህር ጠለል በላይ ከፍታ
        የምግብ ሲናር የደጋ ሰብል ቢሆንም ከእርጥብ ቆላ እስከ ውርጭ ስነምህዳር ባላቸው
        አካባቢዎች መልማት የሚችልና ምርት መስጠት የሚችል እህል ነው፡፡ ሲናር ከባህር
        ጠለል ከ1500-3800 ሜትር ከፍታ ላይ በጥሩ ሁኔታ መመረት ይችላል፡፡ ሰብሉ በደጋ


        አካባቢዎች በስፋት የሚመረት ቢሆንም በቂ ዝናብ በሚያገኙ ቆላማ እና ውርጭማ

        ስነምህዳሮች  ውጤታማ  መሆኑን  በማላመድ  ተግባር  በተሰሩ  ምርምሮች  ማረጋገጥ


        ተችሏል፡፡


        3.2. የአየር ሙቀት
        3.2. የአየር ሙቀት


        የምግብ  ሲናር  ዝቅተኛና  መካከለኛ  የአየርና  የአፈር  ሙቀት  ባለባቸው  አካባቢዎች

        መመረት የሚችል ሰብል ነው፡፡ ሰብሉን ለማምረት የአካባቢ ሙቀት ዝቅተኛና ከፍተኛ


        መጠን  ከ10-25  ዲግሪ  ሴንቲግሬድ  ሲሆን  ለሰብሉ  የተሻለ  ምርት  ተስማሚ  የሆነው

        የሙቀት መጠን ግን በአማካይ 15-22 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነው፡፡


        3.3. የዝናብ መጠን
        3.3. የዝናብ መ ጠን


        የምግብ ሲናር ስንዴና ገብስ በሚመረትባቸው እርጥብ ቆላ እና ውርጭማ አካባቢዎች

        የሚመረት  ሲሆን  ዓመታዊ  የዝናብ  መጠናቸዉ  በአማካኝ  700-1500  ሚ.ሜ  ዝናብ


        በሚያገኙ ስፍራዎች መልማት ይችላል፡፡




                                        የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል     የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   106   107   108   109   110   111   112   113   114   115   116