Page 106 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 106
97
. መ
ቢ
ግ
1 1. መግቢያ
ያ
ሲናር ከብርዕ ሰብሎች የሚመደብ ሲሆን ከገብስና ከስንዴ ጋር የተዛመደና በኢትዮጵያ
አገር በቀል ሰብል ሲሆን ወፍ-ዘራሽ ሲናር (Avena abyssinica) እና አረም ሲናር
ወይንም እንክርዳድ (Avena fatua) የሚጠቀሱ ሲናር ዓይነቶች ናቸው፡፡ እነዚህ አገር
በቀል የሲናር ዓይነቶች ከስንዴና ከገብስ ጋር የሚበቅሉ ሲሆን እነዚህ ዝርያዎች በአርሶ
አደሩ ዘንድ በአረምነት ይታወቃሉ፡፡ በሀገራችን በአርሶ አደሮች እጅ የሚገኙት የሲናር
ዓይነቶች ለመኖነት ከውጭ ሀገር የገቡ ወይም አገር በቀል ዓይነቴዎች ናቸው፡፡ ከወጭ
የገቡት የመኖ ዝርያዎች ለአህል ምርትነት ጥቅም ላይ እየዋሉ ቢሆንም ምርቃቸው
እሾሃማ በመሆኑ በአጨዳና በውቂያ ወቅት የሰውን ቆዳ ስለሚወጉ በአምራቾች ዘንድ
አይወደዱም፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ ሀገራችን የገቡ የምግብ ሲናር ዓይነቶች
እሾሃማ ምርቅ የሌላቸው፤ ምርታማ የሆኑ፤ በንጥረ ነገር ይዘታቸው የበለጸጉና ለአገሮ
እንዱስትሪዎች ግብዓት የሚሆኑ ዝርያዎች ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር
እንስትቲዩት የተለቀቁት የምግብ ሲናር ዝርያዎች ቢኖሩም ወደ ምርት ስርዓቱ
ከማስገባት አንጻር ውስንነት በመኖሩ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ አልተቻለም፡፡
ሲናር የምግብ እና የመኖ ሲናር ተብሎ የሚከፈል ሲሆን የምግብ ሲናር ዘሩ ለምግብነት
ገለባው ደግሞ ለእንስሳት መኖ ያገለግላል። የምግብ ሲናር በአሁኑ ጊዜ በአለም አቀፍ
ደረጃ ለጤና ከሚሰጠው ጥቅም በመነሳት የሰብሉ ተፈላጊነት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ
ይገኛል። በሀገራችንም በደጋማው አካባቢ ሲናርን ለምግብነት በስፋት የሚጠቀሙ
አርሶ አደሮች ቁጥር ቀላል ባይሆንም በተሻሻለ የአመራት ስርዓት ለመደገፍ ፓኬጅና
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል