Page 107 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 107
98
ማንዋል ባለመዘጋጀቱ በሰብሉ መስፋፋትና ምርታማነት ላይ ውስንነት እንደነበረው
ይታወቃል፡፡ የምግብ ሲናር የምግብና ስነ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጠቀሜታ
ካላቸው ሰብሎች መካከል አንዱ ሲሆን በንጥረ ነገር ይዘቱም የበለጸገ እንዲሁም
የተለያዩ ጠቀሜታዎችን የሚያበረክት ሰብል ነው፡፡ ሰብሉን በዘመናዊ የአመራረት
ስርዓት ውስጥ ለማስገባትና በየደረጃው የሚገኘው የኤክስቴንሽን ባለሙያ ግንዛቤ
ይዞ በትክክለኛው የአመራረት ፓኬጅ በመጠቀም መስራት እንዲችሉ ይህን ማኑዋል
ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ብ ሲናር ጠቀሜታ፡-
ግ
የምግብ ሲናር ጠቀሜታ፡-
የም
ለምግብነት
ለምግብነት
የምግብ ሲናር ለምግብና ስነ ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ያለው ጠቀሜታ የጎላ ነው::
ሰብሉ ከሌሎች የብርዕ ሰብሎች ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ የፕሮቲን፣ የማዕድንና የአሰር
ይዘት ስላለዉ ለእናቶችና ለህጻናት አሰፈላጊውን የፕሮቲን ፍላጎት በሟሟላት በኩል
ድርሻው ከፍተኛ ነው፡፡ ሲናር በአገር ዉሰጥ በእንጀራ፣ በቂጣ፣ በገንፎ፣ በአጥሚት፣
በሾርባ እና ለተለያዩ ባህላዊ መጠጥ ዓይነቶች በማዘጋጀት ለምግብነት ያገለግላል፡፡
በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በትላልቅ ሆቴሎችና በሆስፒታሎች የምግብ ዝግጅት ላይ
ጠቀሜታው እየጨመረ በመምጣቱ በምግብ እንዱስትሪዎች በመቀነባበር ላይ ስለሆነ
ሰብሉ ለአግሮ እንዱስትሪዎች ጥሬ እቃ በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል