Page 42 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 42
33
ሻጋታው ስፖሮችን በበሽታው በተበከለው ቅጠል ስር የሚሰራ ሲሆን የስፖሩ ስርጭት መጠንም
እንደ ዝርያው በሽታውን የመቋቋም አቅም ይወሰናል (ምስል 36)፡፡ በሽታው በሚጠቃ ዝርያ
ላይ ከፍተኛ የሆነ የስፖር መፈጠር ቅጠሎችን ግራጫማ ቀለም እንዲይዙ ያደርጋቸዋል (ምስል
37 ሀ እና ለ)፡፡ ነገር ግን በሽታውን በሚቋቋም ዝርያ ላይ ፈንገሱ ሊታይም ላይታይም ይችላል::
በሽታው ተክሉ የአበባ ወይም የዘር ጭንቅላት በሚያወጣበት ወቅት ከተከሰተ፤ የጭንቅላቱ
እድገት ይገታል፣ ጭንቅላቱ የሚይዘው የዘር መጠን ከመቀነሱም በላይ የእያንዳንዱ ዘር መጠንም
አነስተኛ ይሆናል፡፡ የኬነዋው ፍሬ በለጋ ደረጃ ላይ ሲደርስ የአካባቢው ሁኔታ ለበሽታው አመቺ
ከሆነ የሚፈጠሩት ፍሬዎች ይጠቁራሉ፡፡ በሽታውን በሚቋቋሙ ነባር ዝርያዎች ላይ ግን
ሚሊዲው የዘር መጠን ላይ ተጽእኖ አያስከትልም፡፡
ምስል 36.ሚሊዲውን የሚቋቋም ዝርያ (ግራ) በቀላሉ የሚጠቃ ዝርያ በበሽታው እንደተያዘ (መካከለኛ) በመጨረሻ
ቅጠሉ በበሽታው ሲረግፍ (ቀኝ)
ምስል 37. ግራጫማ ስፖሮች በቅጠል የስረኛው ገጽ ላይ (ሀ); ቀይ ቀለም ባላቸው የኬነዋ ዝርያዎች ላይ በታችኛውና
በላይኛው የቅጠል ገጾች ላይ የስፖር አፈጣጠር (ለ)
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

