Page 38 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 38
29
ክሽክሽን በበቂ ሁኔታ ሊቆጣጠሩ የሚችሉ የተፈጥሮ ጠላቶች አሉ፡፡ ነገር ግን ተባዩን ለመቆጣጠር
ሰው ሰራሽ ኬሚካሎች በጥቅም ላይ በሚውሉበት ጊዜ እነዚህ የተፈጥሮ ጠላቶች ላይ ጉዳት
እንዳይደርስ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም የተባይ የተፈጥሮ ጠላቶች ከተክል ተባዮች
የበለጠ በኬሚካል ስለሚጠቁ ነው፡፡ በዚህ አኳያ ለተባይ ቁጥጥር የሚውል ማንኛውም ኬሚካል
መርጦ መግደል የሚችልና ከአካባቢው ቶሎ የሚጠፋ መሆን አለበት፡፡ ከአካባቢ ቶሎ የሚጠፉና
በአካባቢ ላይ ጉዳት ከማያደርሱ ኬሚካሎች ውስጥ አይነተኛ ምሳሌ የሚሆነው ከኒም ዛፍ ፍሬ
ዱቀት የሚዘጋጅ የውሃ ብጥብጥ ነው፡፡ ብጥብጡን ለማዘጋጀት ርጭቱ ከመከናወኑ ከአንድ ቀን
በፊት ፍሬውእንዲደቅ ይደረግና በላስቲክ እቃውስጥ ከ 25 እስከ 50 ግራም የሚሆነው የደቀቀ
ፍሬ በአንድ ሊትር ውሃ ውስጥ እንዲሟሟ ይደረጋል፡፡ በሚሟሟበት ወቅት የተያያዙ ጓጎላዎች
እንዲፈርሱ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ በኋላ ብጥብጡ በጭለማ ውስጥ ከአስራ ሁለት ሰአት
በላይ እንዲቀመጥ ይደረግና በመጨረሻ እየተጣራ ተስማሚ በሆነ ማሳሪያ ይረጫል፡፡
7.2.3. የጎተራ ተባይ
7 . 2 . 3 . የ ጎ ተ ራ ተ ባ ይ
እስከ አሁን ድረስ በየትኛውም የአለም ክፍልምንም አይነት የጎተራ ተባይ በኬነዋ ላይ አልታየም::
ይህም ሁኔታ ከጥራጥሬ ሰብሎች በተለየ መልኩ ኬነዋ አመቱን ሙሉ አማራጭ የፕሮቲን ምንጭ
ሆኖ እንዲያገለግል ያስችለዋል፡፡ ምንም እንኳን ጥራጥሬዎች አነስተኛ ገቢ ላላቸው አርሶ አደሮች
አይነተኛ የፕሮቲን ምንጭ በመሆን ቢያገለግሉም፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ መሉ በሙሉ የምርት
ውድመትን ሊያስከትሉ በሚችሉ የተለያዩ አይነት የጎተራ ተባዮች ይጠቃሉ፡፡ ስለዚህ የስነ
ምህዳርና የምርት አቀማመጥ ሁኔታ ልዩነት ሳይወስነው ኬነዋ አስተማማኝ የሃይልና የንጥረ ነገር
ምንጭ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል