Page 36 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 36

27
        ክንፍ ያወጡና ለመንቀሳቀስና ለመመገብ በቂ ቦታ ወዳለበት የማሳ ክፍል ወይም ወደ ሌላ ማሳ

        ይበራሉ፡፡ ምንም እንኳን ይህ ተባይ በማንኛው የተክል እድገት ደረጃ ላይ ሊከሰት ቢችልም

        በተለየ  ሁኔታ  ለጋ  ቅጠሎችን፣  እንቡጦችንና  ቀንበጦችን  ያጠቃል፡፡  ነገር  ግን  የተባዩ  ቁጥር

        በጣም ከፍ በሚልበት ጊዜ ከመሬት በላይ ባለ በማንኛውም የተክል ክፍል ላይ ሊመገብ

        ይችላል::  ከፍተኛ  ጥቃት  የደረሰባቸው  ቅጠሎች  በወስጣቸው  የሚገኘው  ፈሳሽ  ንጥረ  ነገር

        ስለሚሟጠጥ ተባዩ በሰፈረበት በኩል በመጠቅለል ተባዩን ይሸፍኑታል (ምስል 31 እና 32)::

        ተባዩ  በሰብሉ  የመጀመሪያ  የእድገት  ደረጃ  ወቅት  ከተከሰተ  የቅጠል  መጠውለግና  አጠቃላይ
        የተክል መቀንጨርን ያስከትላል:: በዚህ ተባይ በጣም የተጠቁ ቅጠሎች በመጀመሪያ በቢጫ

        ነጠብጣብ  ይሸፈኑና  እንዚህ  ነጠብጣቦች  እየሰፉ  ሄደው  እርስ  በእርስ  ሲገናኙ  ቅጠሉ  ሙሉ

        በሙሉ  ቢጫ  ይሆንና  ጠውልጎ  ይረግፋል::  ክሽክሾች  መጣጭ  ተባዮች  ስለሆኑ  ከሚመገቡት

        ውስጥ  ትርፍ  የሆነውን  ስኳር  መልሰው  ወደ  ቅጠሉ  የላይኛው  ክፍል  ላይ  ያከማቻሉ

        (ያስወግዳሉ)::  ይህ  ትርፍ  ስኳር  ጥቁር  ሻጋታ  እንዲበቅል  ስለሚያደርግ  የቅጠሎችን  ምግብ

        የማዘጋጀት  ብቃት  ይቀንሳል::  በተጫሪም  ክሽክሾች  በሚመገቡት  ወቅት  ከአንድ  ተክል  ወደ

        ሌላ ተክል የቫይረስ በሽታን ያስተላልፋሉ:: ይህ ቫይረስ በተክሉ የመጀመሪያ የእድገት ደረጃ
        ወቅት  ከሆነ  የተከሰተው፤  ሊገለው  ወይም  ምንም  ምርት  እንዳይሰጥ  ሊያደርገው  ይችላል፡፡

        ተባዩ ደረቅና ሞቃታማ ወቅትን ስለሚመርጥ በመስኖ በሚመረቱ ሰብሎች ላይ የበለጠ ጥቃት

        ያደርሳል፡፡ በዝናብ ወቅትም ቢሆን ከአስር እስከ አስራ አምስት ቀናት የሚቆይ ደረቅ ወቅት

        ከተፈጠረ ተባዩ ሊከሰት ይችላል::

















 የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል  የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   31   32   33   34   35   36   37   38   39   40   41