Page 41 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 41
32
ተዋህስ እንዲያድግለማድረግ በቂ ናቸው፡፡ ዝናብ የሌለበት ደመናማ ወቅትም ለበሽታው
መከሰት ተስማሚ ሊሆን ይችላል፡፡ እርጥበት እስካለ ድረስ በሽታው ከ 0 እስከ 25 ዲ.ሴ
በሆነ የአየር ሙቀት ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡ ከፍተኛ የዝናብ መጠን ባለባቸው አካባቢዎች
ይህ በሽታ ኬነዋን ለማምረት አይነተኛ ማነቆ ነው፡፡ በመሆኑም እንደ ቦሊቪያ ባሉ ዋና ኬነዋ
አምራች ሃገሮች ለውጭ ሃገር ገበያ የሚመረት ኬነዋ ዝቅተኛ የዝናብ መጠን (200- 250 ሚ.ሜ)
ባላቸው አካባቢዎች ብቻየተወሰነ ነው፡፡
የበሽታው ምልክቶች
የ በ ሽ ታ ው ምል ክ ቶ ች
ምንም እንኳን የበሽታው ምልክት በግንድ፣ በቅርንጫፍ በአበባና በፍሬ ላይ የሚታይ ቢሆንም
በሽታው በዋነኛነት የሚያጠቃው ቅጠልን ነው፡፡ እንደ ተክሉ ዝርያ አይነት ቢጫ፣ ሃምራዊ፣
ቀይ፣ ብርቱካናማ ወይም ግራጫ ቀለምያላቸው ትንንሽና ቅርፅ የሌላቸው ነጠብጣቦች መፈጠር
በቅጠሎች ላይ የሚታይ የበሽታው የመጀመሪያ ምልክት ነው (ምስል 35)፡፡ በሽታው እየበረታ
ሲሄድ እነዚህ ነጠብጣቦች ይገጥሙና ቅጠሉ ወይቦ ይረግፋል፡፡ ሁኔታዎች ለበሽታው አመቺ
ከሆኑ (ከፍተኛ የአየር እርጥበት፣ ደመናማና ዝናባማ ቀን) ሁሉም የተክሉ ቅጠሎች ታመው
ሊረግፉና ማንኛውም አይነት የተክል እድገት ሊቆም ይችላል፡፡
ምስል 35. ቀለማቸው እንደ ኬነዋው ሰብል ዝርያ የሚለያይ በሚልዲው ምክንያት በቅጠሎች ላይ
የሚታዩ የበሽታ ምልክቶች
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል